Logo
YenetaTube
የሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ ኮሙኒኬሽን የሐምሌ 2018 ዓ/ም መረጃ እንደሚያመላክተው በወረዳው በተከሰተ ድርቅ ምክንያት

👉 14ሺህ 89 የቁም እንስሳቶች ሞተዋል።

👉 ከ3ሺህ በላይ ነዋሪዎች አካባቢያቸውን ለቀው ተሰደዋል።

👉 በወረዳው ከሚገኙ 24 ቀበሌዎች መካከል 10 ቀበሌዎች ማለትም እርን፣በተል፣በስቂያ፣መረው ብላ፣ መረው ገብርኤል፣ አገጣ፣ ደረባ፣ከረዋ፣ነጋዴ መሻገርያ እና አተባ ቀበሌዎች እስከ ሐምሌ መጨረሻ አካባቢ ምንም ዝናብ ያላገኙ ናቸው።

👉 6 ቀበሌዎች ማለትም አቁና፣ ግልቤና፣ ጣራ፣አዲ ምህረት፣ጭንፍራ እና ጤበላ ዝቅተኛ የዝናብ መጠን እያገኙ ሲሆን፣ቀሪዎቹ 8 ወረዳዎች ደግሞ ጥሩ ዝናብ እያገኙ እንደሆነ መረጃው ያሳያል።

👉 በወረዳው የተለያዩ ሰብሎችን መዝራት የሚቻለው ከባለፈው ሚያዚያ ወር ጀምሮ እንደነበር ቢነገርም ወቅቱን ጠብቆ በአርሶ አደሩ ሰብል የተሸፈነ 9ሺ 88 ሄክታር መሬት በድርቅ ሳቢያ ምንም አይነት ሰብል ማብቀል ሳይችል በመቅረቱ ለኪሳራ ዳርጓል።

👉 በድርቁ ምክንያት 592 አባውራዎችና 305 እማ ውራዎች በአጠቃላይ 3ሺህ 386 ሰዎች መኖሪያ ቀያቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ሆኗል።

👉 የ DW AMHARIC መረጃ እንደሚያመላክተው ደግሞ በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በስቂያ ቀበሌ በምግብ እጥረትና በወረርሽኝ ምክንያት 35 ሰዎች ሲሞቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መሰደዳቸውን ፣ በወረዳው አገጣ ቀበሌ ደግሞ 8 ሰዎች መሞታቸውን ከአካባቢው ነዋሪዎች አረጋግጧል።

በዚህ ዘገባ የጠለምት ወረዳ አደጋ መከላከልና ቅድመ ማስጠንቀቂያ በወረዳው በድርቁ ምክንያት 14ሺ 88 እንስሳት መሞታቸውን ሲያረጋግጥ በድርቁ ምክንያት የሞተ ሰው እንደሌለ አረጋግጧል።

👉 የአዲስ ማለዳ መረጃ እንደሚያመላክተው ደግሞ በጠለምት ወረዳ መረው ቀበሌ በድርቁ ምክንያት እስካሁን 16 ሰዎች መሞታቸውንና በመቶ የሚቆጠሩ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው ተሰደዋል።

👉 ዜጎችን ከድርቁ ለመታደግ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመላክታሉ። ከመንግስት እና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ሰብዓዊ አቅርቦት እንደሚያስፈልግ እየተነገረ ይገኛል። ይሁን እንጅ አሁንም ድረስ የድርቁ አሳሳቢነት እና እያደረሰ ያለው ጉዳት ትኩረት አልተሰጠውም።

በሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ ፣ በየዳ፣ አዲ አርቃይና ደባርቅ ወረዳዎች በድርቁ ከተጎዱ ወረዳዎች መካከል የሚገኙ ሲሆኑ በዋግኽምራ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች የተከሰተው ድርቅ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም መረጃዎች ያመላክታሉ።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.