Logo
FIDEL POST NEWS
አቶ ታዬ ደንደአ “ ሦስት አዳዲስ  ተደራራቢ የወንጀል ክሶች እንደተከፈተባቸው ” ጠበቃቸው ተናገሩ

ዛሬ ባስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግሥት እና በሕገ መንግሥት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ችሎት የቀድሞው ምክትል የሰላም ሚኒስትር ታዬ ደንደአ ሦስት አዳዲስ ተደራራቢ ክሶች በዐቃቤ ህግ እንደተከፈተባቸው ጠበቃቸው አበራ ንጉስ ለአዲስ ማለዳ ነግረዋታል፡፡

አንደኛው “ መንግስትን በኃይል ለመጣል በሚደረግ ዝግጅት ላይ ጫካ ካሉት ኃይሎች ጋር ተመጋጋቢ የሆኑ ፕሮፓጋንዳ ፈጽመዋል፤ የፕሮፓጋዳ ድጋፍ አድርገዋል ” የሚል ሲሆን ይህንን ድጋፍ ያደረጉት ደግሞ ሆርን ኮንቨርሴሽን በሚባል የዩቱብ ቻናል ላይ ቀርበው በሰጡት በሦስት ተከታታይ ክፍሎች በተሰራጨው ዝግጅት ላይ ነው፡፡

ሁለተኛው ክስ ደግሞ በተመሳሳይ በተጠቀሰው የዩቱብ ቻናል ላይ መከላከያ ሠራዊት በተለይም ስለሰሜን ዕዝ ጥቃትና ተያያዥ ጉዳዮች  በተመለከተ “ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሉኝ ብለው የተናገሩት በመከላከያ ላይ የተነዛ ሀሰተኛ መረጃ ነው ” በሚል ሲሆን ሦስተኛው ክስም በዚሁ ቻናል በሰጡት አስተያየት ላይ የተመሰረተ ነው፡፡

ታዬ “ ብልጽግና የአንድን ሰው ስልጣን ለማቆየት የተደራጀ ፓርቲ ነው፤ ፓርቲው በአመዛኙ የማፊያ ባህሪ ያለው መንግስት እንዲመሰረት አስተዋጽዖ ያደረገ እንጂ የህዝብን ፍላጎት ለማስፈጸም የተደራጀ ፓርቲ አይደለም፣ በማለት በሀገሪቱ ህገ መንግስት መሰረት የተመረጠውን መንግስት ስም  በማጉደፍ” በሚል ተከስሰዋል፡፡

በእነዚህ ተደራራቢ ክሶች ላይ መቃወሚያ ላይ ለማቅረብና ውሳኔ ለመስጠት ለህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ቀጠሮ መሰጠጡንም ተናግረዋል፡፡
   
አዲስ ማለዳ
11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.