ሀሰተኛ መረጃ‼️
ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በእስር ያሉ ሰዎች “ በይቅርታ ሊፈቱ ነው ” በሚል እየተሰራጨ ያለው መረጃ “ ሐሰተኛ ነው ” ሲሉ ጠበቃቸው ተናግሯል‼️
ፖለቲከኞችና የማህበረሰብ አንቂዎችን ጨምሮ ጋዜጠኞች እንዲሁም ሌሎች በአማራ ክልል በተቀሰቀሰው በትጥቅ የታገዘ ግጭት ጋር በተያያዘ በእስር ላይ የሚገኙት ግለሰቦች ከእስር ሊፈቱ ነው መባሉን የእነ ክርስቲያን ጠበቃ ሰለሞን ገዛኸኝ “ ሐሰተኛ ነው ” ሲሉ ውድቅ አድርገውታል፡፡
እየተሰራጨ በሚገኘው መረጃ ይፈታሉ ከተባሉት መካከል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ክርስቲያን ታደለ የሚገኙበት ሲሆን ከመጪው ገና በዓል በፊት ከእስር እንደሚፈቱ እንደሚጠበቅም በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እየተሳጩ የሚገኙት መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በእርግጥ መንግስት ከዚህ ቀደም በ2014 የገና በዓል እንደ እስክንድር ነጋ፣ ጀዋር መሐመድ፣ ስብሃት ነጋን ያሉትን ጨምሮ ሌሎችንም ፖለቲከኞች በተመሳሳይ በበዓሉ ዕለት እንደለቀቃቸው ይታወሳል፡፡
ጠበቃ ሰለሞን ሐሰተኛ ናቸው ያሏቸው መረጃዎች ግን በመጀመሪያ ዙር ከእስር ይፈታሉ ተብሎ ከሚጠበቁት መካከል ዮሐንስ ቧያለው፣ ጋዜጠኛ ዳዊት በጋሻው፣ ክርስቲያን ታደለ፣ ሲሳይ አውግቼው፣ ቴዎድሮስ ኃይለማርያም፣ ወንድወሰን አሰፋ፣ መስከረም አበራ፣ ጫኔ ከበደ እና ካሳ ተሻገር እንደሚገኙበት ተመላክቷል፡፡
በሌላ በኩል የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በእነ ዮሐንስ ቧያለው መዝገብ በክርስቲያን ታደለ ላይ ከመጋረጃ ጀርባ የቀረበውን ምስክር ተከትሎ በዐቃቤ ህግ ባቀረበው ሰነድ ላይ አስተያየት ለመስጠት ለጥር 8 ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱ ይታወሳል።
Via : አዲስ ማለዳ
seledadotio

5 months ago