Logo
SeledaPost
100 ቢሊዮን ብር መዘረፉ ከተጋለጠ በኋላ ሚዲያዎች በፓርላማ እንዳይዘግቡ ተከለከለ!

ሪፖርተር ጋዜጣ በትናንት እትሙ ባለስልጣናት እና አርቲስቶች 98 ቢሊዮን ብር መመዝበራቸውን መዘገቡ መነጋገሪያ ሆኖ ውሏል፡፡

98 ቢሊዮን ብር ማለት የኢትዮጵያ አመታዊ በጀት አምስት በመቶ እንደማለት ነው፡፡

ይህ መረጃ መጋለጡን ተከትሎ ሚዲያዎች ላይ ክልከላ ተጥሏል፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያቀርበው የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ ላይ መንግስታዊ ያልሆኑ የግል መገናኛ ብዙኃን ተገኝተው እንዳይዘግቡ ከልክሏል፡፡

የግል መገናኛ ብዙኃን ጋዜጠኞች የመግቢያ በር ላይ መግባት አትችሉም ተብለው ሲከለከሉ እንደ ብሔራዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ እና ኦ.ቤ.ኤን ያሉት ግን ተፈቅዶላቸው መግባታቸውን የአዲስ ማለዳ ሪፖርተር ተመልክቷል፡፡

ይህ ውሳኔ የቋሚ ኮሚቴው ውሳኔ ስለመሆኑም ለጋዜጠኞቹ ተነግሯቸዋል፡፡

በተመሳሳይ ዛሬ ከሰዓት ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው የጤና ሚኒስቴር የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገም ለግል ሚዲያዎች ክፍት ይደረጋል ወይስ እንደ ገንዘብ ሚኒስቴር ክልከላ ይጣልበታል በሚል በስፍራው ከነበሩ ዘጋቢዎች በኩል ለምክር ቤቱ ጥያቄ ቢቀርብም እናሳውቃለን የሚል ምላሽ ከማግኘት ባለፈ ይሁንታ አልተገኘም፡፡

seledadotio
seledadotio
1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.