6 months ago
በአዲስ አበባ በ3 ቀናት ውስጥ 215 አሽከርካሪዎች በ’ጠጥቶ ማሽከርከር’ ተቀጡ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ እየተተገበረ ባለው የመንገድ ደህንነት ንቅናቄ፣ ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ ጠጥተው ሲያሽከረክሩ የተገኙ 215 አሽከርካሪዎች ላይ ጠንከር ያለ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን አስታወቀ።
እንደ ባለስልጣኑ ገለጻ፣ እርምጃው የተወሰደው በአዲሱ ደንብ ቁጥር 557/2016 መሰረት ሲሆን፣ ጥፋቱ በ"ልዩ ደረጃ" ተመድቦ የገንዘብ ቅጣት ተጥሎባቸዋል። የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ገነት ዲባባ እንደገለጹት፣ ቁጥጥሩ የተካሄደው በተመረጡ ሶስት ክፍለ ከተሞች ላይ ባተኮረ የድንገተኛ ኦፕሬሽን ነው።
የቁጥጥር ውጤቱ በየቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ፦
* በቦሌ ክፍለ ከተማ፦ ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 10 ሰዓት በተደረገ ፍተሻ 1,376 አሽከርካሪዎች በትንፋሽ መመርመሪያ መሳሪያ የተመረመሩ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 107ቱ ከሕግ አግባብ በላይ ጠጥተው ተገኝተዋል።
* በጉለሌ ክፍለ ከተማ፦ በአዲሱ ገበያ አካባቢ በተካሄደ ጥብቅ ቁጥጥር 72 አሽከርካሪዎች የእርምት እርምጃ ተወስዶባቸዋል።
* በየካ ክፍለ ከተማ፦ በወሰን መስመር 675 አሽከርካሪዎች ተፈትሸው፣ 34ቱ በሊትር ከ0.24 ሚሊግራም በላይ የአልኮል መጠን በደማቸው ውስጥ ተገኝቶ ቅጣት ተጥሎባቸዋል።
ይህ "የጥር ወር የመንገድ ደህንነት ንቅናቄ" ግንዛቤ ከመፍጠር ባለፈ፣ ለትራፊክ አደጋ ዋነኛ መንስኤ በሆነው ጠጥቶ ማሽከርከር ላይ ያነጣጠረ ሲሆን፣ ቁጥጥሩ እስከ ጥር 30 ድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል። አሽከርካሪዎች ለራሳቸውም ሆነ ለሌሎች ደህንነት ሲሉ ከእንዲህ አይነት አደገኛ ድርጊት እንዲታቀቡም ጥሪ ቀርቧል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#bisrat tv #getutemesgen #getu #ጌጡ #የመንገድደህንነት #አዲስአበባ #ትራፊክማኔጅመንት #ኢትዮጵያ #roadsafety #addisababa

Comments