2 months ago
የወንድማችን እጅጉ አበበን ሕይወት ለመታደግ
የተዘረጋ የረድኤት ጥሪ
#ethiopia | "ሰው ለሰው መድኃኒቱ ነው!" በሚለው እሴታችን መሠረት ወገንን የመርዳት ሌላው ታላቅ የሰብዓዊነት ጥሪ ቀርቧል።
በትውልድ ቦታው በከፋ ዞን ጠሎ ወረዳ እንዲሁም በአሁኑ ወቅት በቤንች ሸኮ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ውስጥ በከፍተኛ የሲስተም አስተዳዳሪነት ሙያ ሕዝብና ሀገሩን በቅንነትና በታማኝነት ሲያገለግል የቆየው ወንድማችን እጅጉ አበበ በአሁኑ ወቅት በብርቱ የጤና እክል ላይ ይገኛል።
ወንድማችን እጅጉ አጋጥሞት ከሚገኘውና እጅግ አስቸጋሪ ከሆነው የካንሰር ሕመም ጋር ብርቱ ትግል እያደረገ ይገኛል።
ሕመሙ ባስከተለበት ከባድ ስቃይና መክበድ ምክንያት በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ አልጋ ላይ ውሎ ሕክምና መከታተል ከጀመረ ከአራት ወራት በላይ ተቆጥረዋል።
በዚህም የሕክምና ቆይታው ወቅት እጅግ አድካሚና ከባድ የሆኑትን የኬሞቴራፒ እና የጨረር ሕክምናዎችን በመከታተል ላይ ይገኛል።
ይህ ፈታኝ ወቅት የእጅጉን አካላዊ ጥንካሬና ጤንነት ብቻ ሳይሆን የጠቅላላ ቤተሰቡን ሕልውና የፈተነ ሆኗል።
እጅጉ የታማሚነትን ስቃይ በጽናት እየተጋፈጠ ያለው የራሱን ሕይወት ለማዳን ብቻ ሳይሆን ከጀርባው የሚጠብቁትንና የእሱን እጅ የሚያዩትን የሁለት ንጹሐን ሕፃናት ልጆቹን ብሩህ ተስፋና የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለመታደግ ጭምር ነው።
የአንድ አባት መውደቅ የቤተሰብ ሕልውና መናጋት ከመሆኑም በላይ የሕፃናቱንም ብሩህ ተስፋ የሚያጨልም በመሆኑ ዛሬ እጅጉና ልጆቹ የእኛን የሁላችንንም የትብብርና የደግነት እጅ አጥብቀው ይሻሉ።
የለመድነውን መልካም ትብብራችንን እና የወገን ደራሽነት ባህላችንን በተግባር የምናሳይበት ሰዓት አሁን ነው።
የቻልነውን ያህል በገንዘብ ካልሆነም ይህንን የረድኤት መልዕክት በተለያዩ ማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ በማጋራት ለታማሚውና ለቤተሰቡ ደራሽ እንድንሆን ጥሪ ቀርቧል።
የእኛ ጥቂት ሳንቲም ለዚህ ቤተሰብ ታላቅ ተስፋና የሕይወት መተርፊያ ናት።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000235379043
እጅጉ አበበ አዋጎ
ስልክ ቁጥር 0917254790
#የህይወትአድንጥሪ #የካንሰርህክምና #ጥቁርአንበሳሆስፒታል #የደግነትእጅ #ከፋ #ቤንችሸኮ #ሰብአዊነት #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

9 months ago
የቀይ ውሃ ፏፏቴ! ሲዝ ከተማ አስተዳደር
#ethiopia | የኢትዮጵያ ጥልቅ የተፈጥሮ ውበት ምንጭ የሆነ ቦታ... የቀይ ውሃ ፏፏቴ!
ይህ ድንቅ ስፍራ ከሚታወቁት መስህቦች ፍጹም የተለየ ነው። የሚገኘውም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በቤንች ሸኮ ዞን፣ ሲዝ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ነው።
ጥቅጥቅ ካለው ደን የሚመጣው የወፎች ዝማሬ እና በሁለት አቅጣጫ የሚፈሰው የውሃ ድምፅ ተደምረው፣ መንፈስን የሚያረጋጋና ከጭንቀት ነጻ የሚያደርግ ፍጹም ሲምፎኒ ይፈጥራሉ።
በሁለት ቦታዎች እየተንዠረገገ የሚፈሰው ፏፏቴው፣ እጅግ በጣም ልዩና ዓይንን የሚማርክ የፎቶ ማንሻ ስፍራን ፈጥሯል።
እዚህ ቦታ ሲደርሱ፣ ልክ እንደ አዲስ የተገኘች ምድር ሰላም ይሰማችኋል። ኢትዮጵያ በውስጧ እንዲህ ያሉ መካነ ሰላም የሆኑ ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታዎች አሏት!
ከቤንች ሸኮ ዞን መቀመጫ ሚዛን አማን ከተማ 52 ኪ.ሜ ከተጓዙ በኋላ ወደ ሲዝ ከተማ ተጠግተው (7 ኪ.ሜ) ሲጓዙ ይህንን ድንቅ ስፍራ ያገኙታል።
#ኢትዮጵያ #የቀይውሃፏፏቴ #የተፈጥሮውበት #ቤንችሸኮ #ሲዝ #ሚዛንአማን #የኢትዮጵያጉዞ #አዲስቦታ #ሰላም #ethiopia #keyewehafalls #ethiopiannature #travelethiopia #hiddengem #benchsheko #mizanaman
Mubarek Abebe
ሚዛን ሚዲያና ኮሙኒኬሽን

Comments