20 days ago
የባሕር በር ፍላጎት፤ ለትውልድ ምንዳ እንጂ ዕዳ ላለማውረስ የተጀመረ ጉዞ
********
የአንድ ሀገር ሉዓላዊነት፣ የኢኮኖሚ ነፃነትና የፖለቲካ ልዕልና በጥብቅ ከተፈጥሮ በረከቶችና ከጂኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጥ ጋር የተሳሰሩ በመሆናቸው፤ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስከበርና የሀገርን ክብር ለመመለስ የጀመረችው የባሕር በር ስትራቴጂ ታሪካዊ እርምጃ ነው።
ኢትዮጵያ በተፈጥሮ አቀማመጧ እና በረጅም ታሪኳ የባሕር በር ባለቤት ሆና፣ ሀገረ መንግሥቷም በየጊዜው እየሰፋ በመጣ የመሬትና ተፈጥሯዊ የባሕር ግዛት ባለቤት በመሆን፣ ከተለያዩ ሥልጣኔዎችና መንግሥታት ጋር ዓለም አቀፍ ግንኙነት የመሠረተች ሀገር ነበረች።
ሆኖም ግን የቅኝ ግዛት እንቅስቃሴና በየዘመናቱ በነበሩ የውስጥና የውጭ የሴራ ኃይሎች ምክንያት፣ ላለፉት ዓመታት የባሕር በር አልባና የሌሎች ጎረቤት ሀገራት ጥገኛ እንድትሆን ተደርጋ ቆይታለች።
ይህም ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላትን ሀገር ለከፍተኛ የኢኮኖሚ ኪሳራና ለደህንነት ስጋት የዳረገ ሲሆን፤ በየዓመቱ ለወደብ ኪራይና ለሎጂስቲክስ አገልግሎት በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንድትከፍል በማስገደድ የንግድ ተወዳዳሪነቷንና የኢኮኖሚ ዕድገቷን የያዘ ማነቆ ሆኖ ቆይቷል።
በሕዝብ ገፊነትና በአመራር ሳቢነት እውን የሆነው ሀገራዊ ለውጥ ይህንን የዘመናት እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ ቆራጥ አቋም ይዟል።
በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራው የመደመር መንግሥት፣ የባሕር በር ጥያቄን ማንሳት እንደማይቻልና እንደ ወንጀል ተቆጥሮ የኖረበትን ሥነ-ልቦናዊ ስብራት የቀየረ ስትራቴጂ ቀርጿል።
ስትራቴጂው በሰላማዊ መንገድ፣ በዲፕሎማሲና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ በመመሥረት የተጀመረ ሲሆን፤ ሀገራችንን በጥገኝነት ቀንበር ስር ጠፍረው ለማቆየትና በረብሻ ለማትረፍ የፈለጉ የውስጥና የውጭ ጠላቶችን እቅድ አክሽፏል።
ይህ ስትራቴጂ የኢኮኖሚ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገር ክብርና የማንነት መገለጫ ጭምር ነው። የኢትዮጵያን የባሕር ኃይል መልሶ በማደራጀትና ጠንካራ የባሕር ላይ መከላከያ በመገንባት፣ ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ቀጣና አስተማማኝ የፀጥታና የደህንነት አጋር እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ ያላትን መሪነት በፅኑ መሠረት ላይ ለመጣል መንገድ ከፍቷል።
የኢትዮጵያ ጥያቄ ፍትሐዊና በዓለም አቀፉ የሉላዊነት መርህ ማለትም ሀብትን በጋራና በፍትሐዊነት የመጠቀም እሴት ላይ የተመሠረተ ነዉ።
"ለትውልድ ምንዳ እንጂ ዕዳ አናወርስም" በሚለው ሀገራዊ መርህ መሠረት፣ ይህ የትውልድ የዘመናት ቁጭት የፈታ ታሪካዊ እርምጃ እስከ መጨረሻው ግቡ እንዲደርስ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አንድነትና ቁርጠኝነት ወሳኝ ነዉ።
መላው ሕዝብ አጀንዳውን በባለቤትነት አጥብቆ በመያዝ፣ ኢትዮጵያ የራሷን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር ብቻ ሳይሆን ዓለም ለሁሉም ፍትሐዊ እንድትሆን የራሷን ደማቅ የታሪክ ዐሻራ እንድታስቀምጥና ትውልዱም በታሪክ የባሕር በር በማስገኘት ረገድ በጋራ መትጋት ይገባል።
በብሌን ደምበሎ
#ባሕርበር #ethiopianaccesstothesea #nationalinterest #ethiopianbroadcastingcorporation

2 months ago
የመደመር አንቀጽ
*************
ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምራ በባሕሩ ዳር የተፈጠረች፤ ዕጣ ፈንታዋም ከባሕሩ ጋር የተቆራኘ ሀገር ናት። በቀይ ባሕር ላይ የነበራት ይዞታ፤ ኢትዮጵያን ጠንካራና በጂኦፖለቲካው ውስጥ ተፈላጊ ሀገር ያደርጋት ነበር።
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር ላይየነበራት ይዞታ እየሟሸሸ ሲመጣና፤ በመጨረሻም ሸቀጧን የምታራግፍበት ኩርማን ወደብ እንኳን ማግኘት ያልቻለችበት የታሪክ ሁኔታ ሲፈጠር ኢትዮጵያ በጂኦፖለቲካው ላይ የነበራት ሚና ኮሰመነ፡፡
ኢትዮጵያ በየትኛውም ዓይነት ሁኔታ ከቀይ ባሕር ስትርቅ የምትሟሽሽ፤ ለቀይ ባሕር ስትቀርብ ደግሞ ገናና የምትሆን ሀገር መሆኗን ታሳቢ ያደረጉ አሻጥሮች የዛሬውን እውነታ ሊፈጥሩ ችለዋል።
የአፍሪካ ቀንድ ምንም እንኳን ወሳኝ የጂኦፖለቲካ ሥፍራ ላይ የሚገኝ ቀጣና ቢሆንም፤ በቀጣናው ላይ ያሉት ሀገራት በግጭትና የእርስ በርስ ጦርነት የሚታመሱ፤ ፖለቲካዊ መረጋጋት የሌለባቸው በመሆኑ፤ ደካማና ዘላቂ ጥቅማቸውን ማስከበር የማይችሉ ሆነዋል።
በአንጻሩ ከባሕሩ በሌላው ጎን የሚገኙት የገልፍ ሀገራት፤ በኢኮኖሚ የፈረጠሙ በመሆናቸው፤ ለቀንዱ ሀገራት ጊዜያዊ ጥቅም በመስጠት ብቻ፤ ዘላቂ የሆነና የበላይነታቸውን የሚያረጋግጥ ጥቅም ከቀንዱ እንዲያገኙ አድርጓቸዋል።
የመደመር ትውልድ
ገጽ - 71
#ethiopianbroadcastingcorporation #ethiopia #ኢትዮጵያ ባሕርበር

3 months ago
የመደመር አንቀጽ
የምንገኘው የዓለም ዋነኛ የንግድ ኮሪደር በሆነው ሥፍራ አካባቢ ነው። የቀይ ባሕር አካባቢ የምሥራቁንና የምዕራቡን ዓለም አገናኝ ወሽመጥ ነው። በመሆኑም የአፍሪካና እስያ መገናኛ ድልድይ ነን። ይህንን ግን ለዕድገታችን አላዋልነውም። እንደ ሲንጋፖር ያሉት ሀገራት አካባቢያቸው የሰጣቸውን ትሩፋት ተጠቅመው በልጽገዋል። አካባቢያቸው የሰጣቸውን ተጽዕኖ የመፍጠር ትሩፋት ለዕድገታቸው ግብአት ያደረጉ ሌሎችም በርካታ ሀገራት አሉ። ሀገራችን በአንጻሩ በአፍሪካ ያላትን ተጽዕኖ ለዕድገቷ ግብዐትነት በሚገባ አልተጠቀመችውም።
የመደመር መንግሥት
ገጽ 53
Ethiopian Broadcasting Corporation #ethiopia #medemer #ebc #ቀይባሕር #የባሕርበር

Comments