18 days ago
(ዘ-ሐበሻ መዝናኛ ዜና) ኪነ-ጥበብ ድንበር የለውም፤ የሀገርን ማንነት፣ ባህልና ታሪክ ተሸክሞ የዓለምን ማዕዘናት ሁሉ ያቋርጣል። አሁን ደግሞ ተራው የኢትዮጵያ ሲኒማ ሆኗል። በዳይሬክተር አብርሃም ገዛኸኝ ልዩ ጥበባዊ እይታ እና በፕሮዲውሰር ታማራ ማርያም ዳዊት ስልታዊ ዝግጅት የተጠነሰሰው «መሀል ሰፋሪ» የተሰኘው አዲስ የኢትዮጵያ ፊልም፣ በዓለም ፊልም ኢንዱስትሪ ውስጥ እጅግ ስመ-ጥር በሆነው በ83ኛው የቬኒስ ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫል ላይ በኩራት እንዲመረጥ ሆኗል። ይህ ምርጫ ተራ ስኬት አይደለም፤ ፊልሙ በፌስቲቫሉ እጅግ ተፈላጊ በሆነው "Final Cut" መርሃ ግብር ላይ ከተመረጡ ስድስት ምርጥ የመጀመሪያ ደረጃ ኤዲቲንግ ረቂቅ ፊልሞች መካከል አንዱ መሆን መቻሉን የሚያበስር ትልቅ የታሪክ ምዕራፍ ነው።
ይህ ጥበባዊ ፍጥረት በመጪው መስከረም ወር ማራኪ ውበት ወደተላበሰችው የጣሊያን ምድር በመጓዝ፣ ለዓለም አቀፍ የፊልም ባለሙያዎች፣ የፊልም ሽያጭ ድርጅቶች፣ አከፋፋዮችና አዘጋጆች ለእይታ ይበቃል። መድረኩ በመጀርያ ደረጃ ኤዲቲንግ ላይ ለሚገኙ የፈጠራ ሥራዎች የድህረ ፕሮዳክሽን ሥራዎቻቸውን በከፍተኛ የገንዘብና የቴክኒክ ድጋፍ አጠናቀው ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲገቡ ሰፊ በር የሚከፍት ታላቅ የዕድል ድልድይ ነው። የፊልሙ ፈጣሪዎች የኢትዮጵያን ጥልቅ ታሪክና ባህል ይዘው በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ ለመቅረብ በመቻላቸው የተሰማቸውን ታላቅ ኩራትና የላቀ ደስታ ሲገልጹ፣ ሥራው እዚህ እንዲደርስ ከጎናቸው ለቆሙትና በሀገራችን የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንደ "በስንቱ" እና "የእግር እሳት" ባሉ ተወዳጅ ድራማዎች ስሙ በግንባር ቀደምትነት ለሚነሳው አብሪኮም መልቲሚዲያ፣ እንዲሁም ለጎበዝ፣ ቱ ፓይለትስ፣ ባሬንትስ እና ኒው አምስተርዳም የፊልም ኩባንያዎች የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የአንድ ፊልም ነፍስ በገጸ-ባህሪያቱ ውስጥ በሚነፍሱ ተዋናዮች ላይ የተመሠረተ ነው። «መሀል ሰፋሪ» በሀገራችን የኪነ-ጥበብ አድማስ ውስጥ ትልቅ ክብርና ተወዳጅነትን ያተረፉትን የነጋሲዎቹን ተዋናዮች ብቃት ይዞ ብቅ ብሏል። ታዋቂዎቹ አርቲስቶች ግሩም ዘነበ፣ አበበ ባልቻ እና ፀደይ ፋንታሁን በፊልሙ ላይ ላሳዩት ወሳኝና ተደናቂ አስተዋጽኦ የፊልሙ አዘጋጆች ትልቅ አድናቆት የቸሯቸው ሲሆን፣ የእነሱ ድንቅ አተዋወን ፊልሙን ዓለም አቀፍ መስፈርት እንዲያሟላ ማድረጉም ይነገራል።
እ.ኤ.አ በ1932 የተመሠረተው የቬኒስ የፊልም ፌስቲቫል በዓለም ላይ ካሉ እጅግ አንጋፋና ጥንታዊ መድረኮች አንዱ እንደመሆኑ መጠን፣ «መሀል ሰፋሪ» በዚህ መድረክ ላይ መመረጡ የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ወደ አዲስ ከፍታ እየተጋገዘ መሆኑን ያበስራል።
በሀገር ውስጥ የጥበብ አሻራውን እያኖረ ያለው አብሪኮም መልቲሚዲያ እና ቡድኑ በጣሊያን መድረክ ላይ የኢትዮጵያን ስም ከፍ አድርገው ለማንሳትና የሀገራችንን ታሪክ ለዓለም ለማስተዋወቅ በጉጉት መስከረምን እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

3 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢቢኤስ ቴሌቪዥን 33 ሚሊዮን ብር እንዲታገድ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳለፈ፡፡ በከሳሽ አብሪኮም መልቲሚዲያና በተከሳሽ ሲልቨርስፕሪንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር መካከል ለተነሳው ክርክር ፍርድ ቤት ውሳኔ መስጠቱን ለዘሀበሻ የደረሰው መረጃ ያሳያል፡፡ ለሁለቱ ድርጅቶች ክስ ምክንያት የሆነው በስንቱ የተሰኘው ተከታታይ ድራማ ነው፡፡
የበስንቱ ድራማ ባለቤት የሆነው አብሪኮም ለመልቲሚዲያ ለፌዴራል ፍርድ ቤት ልደታ 1ኛ ንግድና ኢንቨስትመንት ፍትሀ ብሄር ችሎት ባቀረበው አቤቱታ ተከሳሹ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ያለ አግባብ ላሰራጨው የኦዲዮ ቪዥዋል ስራ የጉዳት ካሳ እንዲከፈለው ጠይቋል፡፡ በመሆኑም ይህ ካሳ እስኪከፈለው ድረስ በፍትሀ ብሄር ስነስርአት ቁጥር 154 መሰረት እስከ 33 ሚሊዮን 128 ሺህ 115 ብር እንዲታገድለት ጥያቄ ማቅረቡን የውሳኔ ግልባጩ ያሳያል፡፡
ተከሳሽ አቤቱታው ከደረሰው በኋላ ክርክር ያደረገ ሲሆን ፍርድ ቤቱም ግንቦት 4 ቀን 2018 በጉዳዩ ላይ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ በውሳኔውም ጉዳዩ በክርክር ላይ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ‹‹ተከሳሽ በክርክሩ ቢረታ ገንዘቡን ሊያሸሽ የሚችልበት እድል ከፍተኛ መሆኑን በማስገባት›› እግዱ እንዲሰጥ መወሰኑን ለመረዳት ችለናል፡፡ ፍርድ ቤቱ ባስላለፈው ትእዛዝም ከተከሳሽ ማለትም ከኢቢኤስ የባንክ አካውንት ላይ እስከ 33,128,115 ብር ሳይከፈል ታግዶ እንዲቆይና ይህ ትእዛዝም ለሁሉም ባንኮች እግዱ እንዲፃፍ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

#ethiopia | የእንግሊዝ ኤምባሲ ማሳሰብያ በአዲስ አበባ | ሀብታም ለመሆን 4 ጨቅላዎችን ገደለ | የመንግሥት ግዢ ታገደ | በስንቱ ድራማ ታገደ
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
3 months ago
“በስንቱ" ድራማ በቻናል ዋን እንዳይተላለፍ በፍርድ ቤት ታገደ
#fastmereja I ለሦስት ዓመታት በኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የነበረው ታዋቂው "በስንቱ" ድራማ፣ ወደ ቻናል ዋን (Channel 1) ተዛውሮ የመጀመሪያውን ክፍል ካሳየ በኋላ በቀጣይ እንዳይተላለፍ በፍርድ ቤት እግድ ተጣለበት። እግዱ የተላለፈው በኢቢኤስ እና በአብሪኮ መልቲ ሚዲያ መካከል በተፈጠረ የባለቤትነት መብት ክርክር ምክንያት እንደሆነ ታውቋል።
የሁለቱ ተቋማት አለመግባባት ወደ ፍርድ ቤት ማምራቱን ተከትሎ፣ ከሚያዚያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በቻናል ዋን መታየት የጀመረው ድራማው ከአንድ ክፍል በላይ ሊቀጥል አልቻለም። ከእግዱ ጋር ተያይዞ በቀጣይ ሊሰሩ የነበሩ የቀረጻ ስራዎችም ለጊዜው እንዲቆሙ ለአርቲስቶቹ ተነግሯቸዋል።
በሌላ በኩል አብሪኮ መልቲ ሚዲያ በኢቢኤስ ላይ የፍትሐ ብሔር ክስ የመሰረተ ሲሆን፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ችሎት የሁለቱን ወገኖች ክርክር ለመስማት ለግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል ኢትዮጲካሊንክ ነው የዘገበው።

Sponsored by
Surafel
4 months ago
ኢቢኤስ ቻናል ዋንን አስጠነቀቀ!
ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በስንቱ ድራማ የቅጅ መብት ጥሰትን በማስመልከት ለቻናል ዋን ኢትዮጵያ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
ኢቢኤስ ህጋዊ ወኪሉ እንደሆነ በገለጸው ሲልቨር ስፕሪንግ ፕሮዳክሽን እና ፕሮሞሽን በኩል ፤ ቻናል ዋን ጣቢያን በስንቱ ሲትኮም ድራማ ላይ የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ጥሰት እየፈጸመ መሆኑን ጠቁሟል።
ድርጅቱ በጻፈው ደብዳቤ እንዳመለከተው፤ በስንቱ ወይም 'ነፀ ብራቅ' የሚል ስም የሚጠራው ተከታታይ ድራማ ባለቤት እና ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር ኢቢኤስ መሆኑን ገልጿል።
ይህ የኦዲዮ ቪዥዋል ስራ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ተመዝግቦ ህጋዊ ጥበቃ የሚደረግለት መሆኑን አመልክቷል።
የማስጠንቀቂያ ደብዳቤው ሲያብራራም ሲልቨር ስፕሪንግ ቀደም ሲል ካብሪኮ መልቲሚዲያ ጋር በነበረው የስራ ግንኙነት እና የውል ስምምነት መሰረት ስራውን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የማሰራጨት፣ የመጠቀም እና በማንኛውም የቅጂ መብት እና ተዛማጅ መብቶች ላይ ብቸኛ ባለመብት መሆኑን ገልጿል።
ይሁን እንጂ ቻናል ዋን ኢትዮጵያ ድራማውን በጣቢያው ለማሰራጨት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በተለያዩ መንገዶች ማወቁን የገለጸው ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ይህ ድርጊት በህግ ጥበቃ የተሰጠውን መብት የሚጥስ እና የማይተካ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን አስገንዝቧል።
በመሆኑም ቻናል ዋን ከህግ ተቃራኒ ተግባር እንዲቆጠብ እና አፋጣኝ ማስተካከያ እንዲያደርግ እንዲሁም ማስጠንቀቂያውን ተላልፎ እንቅስቃሴውን የሚቀጥል ከሆነ ተገቢውን የህግ ሂደት በመከተል ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል።
seledadotio

የአብሪኮም መልቲሚዲያ እና የቻናል ዋን አዲስ አጋርነት
#ethiopia | በተወዳጆቹ "የእግር እሳት" እና "በስንቱ" የቴሌቭዥን ድራማዎች ስኬታማ የጥበብ ጉዞውን ያስመሰከረው አብሪኮም መልቲሚዲያ፣ አዳዲስ ስራዎችን በጋራ ለመስራት ከቻናል ዋን (Channel 1) ቴሌቭዥን ጋር ስምምነት ላይ ደረሰ።
ጥራት ያላቸውን እና የብዙዎችን ልብ የገዙ ፕሮዳክሽኖችን በማቅረብ የሚታወቀው አብሪኮም፣ በዚህ አዲስ አጋርነት በታሪክ ይዘታቸውና በምስል ጥራታቸው ከፍ ያሉ ድራማዎችን ይዞ ለመቅረብ ተዘጋጅቷል።
እነዚህ አዳዲስና ተወዳጅ ይሆናሉ ተብለው የሚጠበቁ ፕሮግራሞች ከሚመጣው የትንሳኤ በዓል ጀምሮ ለተመልካች መድረስ እንደሚጀምሩ ታውቋል።
ጥበብ እና መዝናኛን አቀናጅቶ በማቅረብ የሚታወቀው አብሪኮም፣ ከቻናል ዋን ጋር በመሆን ምን አይነት አዳዲስ ገጸ-ባህሪያትን እና ታሪኮችን ይዞልን ይቀርብ ይሆን?
በጉጉት እንጠብቃለን!
#abri -comMultimedia #channel1tv #ethiopiandrama #የእግርእሳት #በስንቱ #entertainment #ethiopia #easterspecial

6 months ago
ከነነዌ ሰማይ ስር የወረደ ምሕረት፡ ከጥፋት ማዕበል ወደ ንስሐ ወደብ
ከአንድ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ለፊደል ፖስት የተላከ
በቤተክርስቲያናችን ቀመር መሠረት፣ ዛሬ የነነዌ ጾም ሲጀመር የአዋጅ ነጋሪው ቃል በልባችን ጓዳ ያስተጋባል። የታሪክ መጋረጃ ሲገለጥ፣ በጤግሮስ ወንዝ ዳርቻ ላይ የምትገኘው ታላቋ የነነዌ ከተማ በግርማዋና በውበቷ ትታያለች። ዐሥራ ሁለት ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው ቅጥሯ፣ በንጉሥ ሰናክሬም የታነጹት ግዙፍ ሕንጻዎቿና የንግድ እንቅስቃሴዋ የዓለም ማዕከል አስመስሏታል።
ነገር ግን ከዚህ ውጫዊ ድምቀት በስተጀርባ፣ ከተማዋ በኃጢአት ግነትና በግፍ ደም እየተናወጠች ነበር። እንደ ነቢዩ ናሆም ምስክርነት፣ ነነዌ "የደም ከተማ" ነበረች፤ በሐሰት፣ በቅሚያና በዝሙት የሰከረች (ናሆም 3፡1)።
የኮብላዩ ነቢይና የታላቁ ዓሣ ምሥጢር
እግዚአብሔር አምላክ የፍጥረቱን ጥፋት አይሻምና የነነዌን ሕዝብ ወደ ንስሐ ለመጥራት ነቢዩ ዮናስን አዘዘው። ዮናስ ግን የአሦራውያንን ጭካኔ ያውቅ ነበር። "ብሰብክላቸውና ንስሐ ቢገቡ፣ አንተ ርኅሩኅ አምላክ ስለሆንህ ትምራቸዋለህ፤ እኔም ሐሰተኛ ነቢይ እባላለሁ" በሚል ስጋት ወደ ተርሴስ ኮበለለ። ዮናስ የሰው ልጆችን ጠባይና የአምላኩን ቸርነት እያወቀ፣ በጭካኔ የታወቁት የነነዌ ሰዎች እንዲጠፉ ይፈልግ ነበር።
ነገር ግን ከእግዚአብሔር ፊት መሸሸግ አይቻልም። ማዕበሉ መርከቧን ሲመታ፣ መርከበኞቹ በፍርሃት ተርበደበዱ። ዮናስ ግን በውስጠኛው ክፍል ተኝቶ ነበር። ዮናስ የችግሩ ምንጭ እሱ መሆኑን ሲረዳ ለባልንጀሮቹ እንዲህ አላቸው፦ "ይህ ታላቅ ማዕበል በእኔ ምክንያት በላያችሁ እንደ መጣ አውቃለሁና አንሥታችሁ ወደ ባሕር ጣሉኝ" (ዮናስ 1፡12)።
ዮናስ ወደ ባሕር ተጣለ፤ ነገር ግን ሞት አልተቀበለውም። የእግዚአብሔር ጥበብ ታላቅ ዓሣን አዘጋጅታ ነበር። ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት በዓሣ ሆድ ውስጥ ሆኖ ሲጸልይ፣ ያ በጨለማ የተከበበው ሆድ ለዮናስ የንስሐ ጓዳ ሆነለት።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይህንን ሲያረጋግጥ፦ "ዮናስ በዓሣ አንበሪ ሆድ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ፣ እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት መዓልትና ሦስት ሌሊት ይኖራል" በማለት የትንሣኤው ምሳሌ አድርጎታል (ማቴ. 12፡40)።
የነነዌ ሰቆቃና የንጉሡ አዋጅ
ዮናስ በዓሣው ተተፍቶ ነነዌ ሲደርስ፣ መልእክቱ አጭርና ልብ ሰባሪ ነበረች፦ "በሦስት ቀን ውስጥ ነነዌ ትገለበጣለች!" ይህ ቃል በከተማዋ አውራ ጎዳናዎች ሲስተጋባ፣ የነነዌ ሰዎች ልብ እንደ ሰም ቀለጠ። የከተማዋ ግርማ ሞገስ በድንገት በጭንቀት ደመና ተሸፈነ።
የሚገርመው የታሪኩ ክፍል የነነዌ ንጉሥ ምላሽ ነው። እርሱ እንደ ዘመኑ ነገሥታት በትዕቢት "እኔ ማን ነኝና አምላክ ይገሥጸኛል?" አላለም። ይልቁንም ከዙፋኑ ወረደ፣ ዘውዱን አወለቀ፣ ማቅ ለበሰ፣ በአመድም ላይ ተቀመጠ።
ያ ዝነኛና ጨካኝ ንጉሥ እንዲህ የሚል አዋጅ አወጣ፦
"ሰዎችና እንስሶች፣ ላሞችና በጎች አንዳችን እንኳ አይቅመሱ፤ አይሰማሩም ውኃንም አይጠጡ... ሰዎች ሁሉ ወደ እግዚአብሔር በጽኑ ይጥሩ፣ ሰውም ሁሉ ከክፉ መንገዱና በእጁ ካለው ግፍ ይመለስ" (ዮናስ 3፡7-8)።
ይህ ትዕይንት እጅግ ልብ አንጠልጣይ ነበር። እስቲ በዓይነ ሕሊናችሁ ተመልከቱት፤ ጡት የናፈቁ ሕፃናት ሲያለቅሱ፣ ውኃ የተጠሙ እንስሳት በየሜዳው ሲጮኹ፣ የእናቶች ልቅሶና የአባቶች ዋይታ ሰማይ የደረሰበትን ያንን የጭንቅ ሰዓት። ከተማዋ በሙሉ በታላቅ ሱባኤ ተያዘች። በእግዚአብሔር ፊት የቀረበው ይህ እውነተኛ ጸጸት የሰማይን ደጅ አንኳኳ።
እግዚአብሔርም ንስሐቸውን አይቶ፣ ሊያደርግባት ካሰበው ጥፋት ተመለሰ። ሞት በሕይወት ተተካ፣ ቁጣ በምሕረት ተለወጠ።
ከነነዌ እስከ ዘመናችን፡ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርት
የነነዌ ጾም በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት መሠረት ከዐቢይ ጾም ሁለት ሳምንት ቀድሞ የሚጾም የንስሐ ጅማሬ ነው። ይህ ጾም ለእኛ ለክርስቲያኖች ታላቅ ትምህርት አለው። ዛሬም እንደ ነነዌ ሰዎች ዓለማችን በክህደት፣ በደም መፋሰስና በሥጋዊ ፍላጎት ተጠምዳለች።
በታሪካችን ውስጥ ያለፉት ሥርዓቶች ቤተ ክርስቲያንን ለመደምሰስና አማኞችን ለማሳደድ ቢሞክሩም፣ የነነዌ አምላክ ግን ቤተ ክርስቲያኑን ጠብቆ አቆይቷል። ዛሬም ቢሆን ሀገራችንና ዓለማችን ከገጠማቸው ፈተና የምንወጣው በጦር መሣሪያ ብዛት ወይም በፖለቲካዊ ብልሃት ሳይሆን፣ እንደ ነነዌ ሰዎች በንስሐ ወደ አምላካችን ስንመለስ ብቻ ነው።
ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለው፦ "ኑና እንዋቀስ ይላል እግዚአብሔር፤ ኃጢአታችሁ እንደ አለላ ብትሆን እንደ አመዳይ ትነጻለች" (ኢሳ. 1፡18)። ይህ ጥሪ ዛሬም ለእኛ ነው። ዮናስ ለቅል ተክል ሲያዝን፣ እግዚአብሔር ግን "በቀኝና በግራቸው ያለውን የማይለዩ ከአንድ መቶ ሃያ ሺሕ የሚበልጡ ሰዎችና ብዙ እንስሳት ላሉባት ለታላቂቱ ከተማ ለነነዌ አልራራምን?" በማለት መሐሪነቱን ገልጧል (ዮናስ 4፡11)። ይህም አምላካችን ለሰው ልጆች ሁሉ ያለውን ጥልቅ ፍቅር ያሳያል።
የንስሐ ኃይልና የእንባ በረከት
ንስሐ ማለት "አእምሮን መለወጥ" ማለት ነው። የነነዌ ሰዎች የሰሩትን ግፍ አልካዱም፤ ይልቁንም "በእጃችን ካለው ግፍ እንመለስ" ብለው ተነሱ። ዛሬ የእኛስ እጆች በምን ተለክተዋል? ምላሳችን በስንቱ ስም ማጥፋትና ሐሰት ቆሽሿል? ልባችን በስንቱ ቅናትና ክፋት ታውኳል?
የነነዌ ሰዎች ጾም ልዩ የሚያደርገው የእንስሳቱና የሕፃናቱ ተሳትፎ ነው። ንጹሐኑ ፍጥረታት ስለ በደለኛው ሰው ልጅ ጮኹ። ዛሬም እኛ ስንጾም፣ የግል ሕይወታችንን ብቻ ሳይሆን የማኅበረሰባችንንና የሀገራችንን ሸክም ይዘን መቅረብ ይገባናል። ንስሐ የሰማይ መዝጊያን የምትከፍት ቁልፍ ናት። የነነዌ ሰዎች ለዮናስ ስብከት የሰጡት ፈጣን ምላሽ፣ ዛሬ ለዘመናት በቃለ እግዚአብሔር ለምንመገበው ለእኛ ትልቅ ትምህርት ነው።
ማጠቃለያና ጥሪ
የነነዌ ታሪክ ልብ ወለድ ሳይሆን፣ የእግዚአብሔር መሐሪነትና የሰው ልጅ የንስሐ ኃይል የታየበት እውነተኛ ክስተት ነው። ጾመ ነነዌን ስንጾም፣ እንደ ዮናስ ከእግዚአብሔር ትእዛዝ መኮብለልን ትተን፣ እንደ ነነዌ ሰዎች ደግሞ ከክፉ መንገዳችን ተመልሰን ሊሆን ይገባል። ግፍ፣ ዝሙት፣ መተትና ክፋት በነገሡባት ዓለም ውስጥ፣ መፍትሔው ፖለቲካዊ መግለጫ ሳይሆን እንደ ነነዌ ንጉሥ በማቅና በአመድ ሆኖ ወደ ፈጣሪ መጮኽ ነው።
ያለፈው ታሪካችን በደም የታጠበ ቢሆንም፣ ዛሬ በንስሐ ብንመለስ ግን አምላካችን መዓቱን በምሕረት የሚመልስ ቸር አባት ነው።
የነነዌ ሰዎች አምላክ ሆይ! ለነነዌ ሰዎች የሰጠኸውን የንስሐ ልብ ለእኛም ስጠን። ከጥፋት ማዕበል አውጥተህ ወደ ምሕረትህ ወደብ አግባን።

8 months ago
አብሪኮም መልቲሚዲያ ከኢቤኤስ ቴሌቭዥን ጋር የነበረውን የሥራ ቆይታ አጠናቀቀ።
ለሶስት ተከታታይ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የነበረው ተወዳጁ በስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ፕሮዲዩሰር የሆነው አብሪኮም መልቲሚዲያ፤ ከጣብያው ጋር የነበረውን የሥራ ውል ማጠናቀቁን መልቲሚዲያው አሳውቋል።
አብሪኮም መልቲሚዲያ ከኢቢኤስ ቴሌቭዥን ጋር የነበረው የሥራ ቆይታ መጠናቀቁን ተከትሎ፤ ተወዳጁ በስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ድራማ ከታህሳስ 03 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢቢኤስ ቴሌቭዥን እንደማይተላለፍ እና በበስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ዙሪያ የሚኖሩ ተጨማሪ መረጃዎችን በቅርቡ እንደሚያሳውቅ መልቲሚዲያው ገልጿል።
ከኢቢኤስ ቴሌቭዥን ጋር ሰላማዊ እና ጥሩ የሥራ ቆይታ እንደነበራቸው የገለጸው አብሪኮም፤ ለጣብያው ባለቤቶች እና ሠራተኞች የቀና ምሥጋና አቅርበዋል።

አብሪኮም መልቲሚዲያ ከኢቤኤስ ቴሌቪዥን ጋር የነበረውን የሥራ ቆይታ አጠናቀቀ
#ethiopia | ለሦስት ተከታታይ ዓመታት በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የነበረው ተወዳጁ በስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ፕሮዲዩሰር የሆነው አብሪኮም መልቲሚዲያ፤ ከጣቢያው ጋር የነበረውን የሥራ ውል ማጠናቀቁን መልቲሚዲያው አሳውቋል።
አብሪኮም መልቲሚዲያ ከኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር የነበረው የሥራ ቆይታ መጠናቀቁን ተከትሎ፤ ተወዳጁ በስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ድራማ ከታህሳስ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን እንደማይተላለፍ እና በበስንቱ የቤተሰብ ሲትኮም ዙሪያ የሚኖሩ ተጨማሪ መረጃዎችን በቅርቡ እንደሚያሳውቅ መልቲሚዲያው ገልጿል።
ከኢቢኤስ ቴሌቪዥን ጋር ሰላማዊ እና ጥሩ የሥራ ቆይታ እንደነበራቸው የገለጸው አብሪኮም፤ ለጣቢያው ባለቤቶች እና ሠራተኞች የቀና ምሥጋና አቅርበዋል።

Comments