ኢቢኤስ ቻናል ዋንን አስጠነቀቀ!
ኢቢኤስ ቴሌቪዥን በስንቱ ድራማ የቅጅ መብት ጥሰትን በማስመልከት ለቻናል ዋን ኢትዮጵያ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።
ኢቢኤስ ህጋዊ ወኪሉ እንደሆነ በገለጸው ሲልቨር ስፕሪንግ ፕሮዳክሽን እና ፕሮሞሽን በኩል ፤ ቻናል ዋን ጣቢያን በስንቱ ሲትኮም ድራማ ላይ የቅጂ እና ተዛማጅ መብቶች ጥሰት እየፈጸመ መሆኑን ጠቁሟል።
ድርጅቱ በጻፈው ደብዳቤ እንዳመለከተው፤ በስንቱ ወይም 'ነፀ ብራቅ' የሚል ስም የሚጠራው ተከታታይ ድራማ ባለቤት እና ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲዩሰር ኢቢኤስ መሆኑን ገልጿል።
ይህ የኦዲዮ ቪዥዋል ስራ በኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት ተመዝግቦ ህጋዊ ጥበቃ የሚደረግለት መሆኑን አመልክቷል።
የማስጠንቀቂያ ደብዳቤው ሲያብራራም ሲልቨር ስፕሪንግ ቀደም ሲል ካብሪኮ መልቲሚዲያ ጋር በነበረው የስራ ግንኙነት እና የውል ስምምነት መሰረት ስራውን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር የማሰራጨት፣ የመጠቀም እና በማንኛውም የቅጂ መብት እና ተዛማጅ መብቶች ላይ ብቸኛ ባለመብት መሆኑን ገልጿል።
ይሁን እንጂ ቻናል ዋን ኢትዮጵያ ድራማውን በጣቢያው ለማሰራጨት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን በተለያዩ መንገዶች ማወቁን የገለጸው ሲልቨር ስፕሪንግ፣ ይህ ድርጊት በህግ ጥበቃ የተሰጠውን መብት የሚጥስ እና የማይተካ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን አስገንዝቧል።
በመሆኑም ቻናል ዋን ከህግ ተቃራኒ ተግባር እንዲቆጠብ እና አፋጣኝ ማስተካከያ እንዲያደርግ እንዲሁም ማስጠንቀቂያውን ተላልፎ እንቅስቃሴውን የሚቀጥል ከሆነ ተገቢውን የህግ ሂደት በመከተል ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል።
seledadotio

4 months ago