3 months ago
እየሄዱበት የነበረው መኪና ነዳጅ በመጨረሱ የተሳፈሩበት ሲኖትራክ ተገልብጦ የሰዎች ህይወት አለፈ
📌በቄለም ወለጋ በደረሰ አሰቃቂ የትራፊክ አደጋ የ8 ሰዎች ሕይወት አለፈ
#ethiopia | በቄለም ወለጋ ዞን ሰዮ ደንታ ወረዳ፣ ነዳጅ በጨረሰ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ምክንያት ወደ ጭነት መኪና ተዛውረው ሲጓዙ የነበሩ 8 ሰዎች በደረሰባቸው የመገልበጥ አደጋ ሕይወታቸው ማለፉ ተሰማ።
መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 3፡30 ላይ ከደንቢ ዶሎ ከተማ ወደ አሺ ሙጌ ወረዳ ከ20 በላይ ተጓዦችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ "ዶልፊን" ተሽከርካሪ መንገድ ላይ ነዳጅ ይጨርሳል። በዚህም ምክንያት ተጓዦቹ ጉዟቸውን ለመቀጠል አሸዋ ጭኖ ወደ ሙጊ ከተማ ይጓዝ በነበረ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-35460 ኢቲ በሆነ "ሴኖ ትራክ" የጭነት መኪና ላይ ለመሳፈር ተገደዋል።
የጭነት መኪናው ደንታ ቀበሌ "አባ ጃራ ቀረብቾ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ላይ ሲደርስ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ የሚከተሉት ጉዳቶች ደርሰዋል፦
የ8 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ 6 ወንዶች እና 2 ሴቶች (ሁለቱ ሕፃናት ናቸው) ይገኙበታል።
በ12 ሰዎች ላይ (7 ወንዶች እና 5 ሴቶች) ከባድ የመቁሰል አደጋ ደርሷል።
የዞኑ ፖሊስ ዋና መምሪያ የትራፊክ ደህንነት ቁጥጥር አስተባባሪ ምክትል ኢንስፔክተር ሞቲ ጉዲሳ ለብስራት ሬዲዮ እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው ተጓዦች በደንቢ ዶሎ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
አደጋውን ያደረሰው የሴኖ ትራኩ አሽከርካሪ ለጊዜው ከአካባቢው ቢሰወርም፣ ፖሊስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፍተኛ ክትትል እያደረገ መሆኑ ተገልጿል ሲል የዘገበው ብስራት ኤፍ ኤም ነው።
እንዲህ ያሉ አሳዛኝ አደጋዎች እንዳይደገሙ አሽከርካሪዎች የቴክኒክና የነዳጅ ዝግጅታቸውን አስቀድመው እንዲፈትሹ፣ ተጓዦችም ለጭነት ተብለው በተዘጋጁ መኪኖች ላይ ከመሳፈር እንዲቆጠቡ መልእክት ተላልፏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #trafficaccident #wollega #news #safetyfirst #ቄለምወለጋ #ትራፊክአደጋ

Comments