1 month ago
''የኡጋዱጉ አዛዥ ኢብራሂም ትራኦሬ ሰላም አምጥቷል''ሊቀመንበር ኤቫሪስቴ
#ethiopia | የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር ኤቫሪስቴ ንዳይሺሚዬ በኡጋዱጉ ባደረጉት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት፣ ከቡርኪና ፋሶው መሪ ኢብራሂም ትራኦሬ ጋር በወቅታዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ይህ ስብሰባ በተለይ በሕብረቱ እና በታገዱት የሳሕል ቀጣና ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማደስ አዲስ ተስፋ የፈነጠቀ ሆኗል።
ፕሬዝዳንት ንዳይሺሚዬ፣ መሪው ኢብራሂም ትራኦሬ ለሀገራዊ ሰላምና መረጋጋት እያሳዩት ያለውን "ጽኑ ቁርጠኝነት" በማድነቅ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ሊቀመንበሩ ስለ ሳሕል ቀጣና እና ስለ ቡርኪና ፋሶ ህዝብ ነባራዊ ሁኔታ ካለባቸው የተዛባ ግንዛቤ ወጥተው፣ አሁን "ተጨባጭ እውነታውን" በተሻለ ሁኔታ መረዳታቸውን ገልጸዋል።
ወደ የጋራ መጻኢ እድል በጋራ ለመጓዝ የሚያስችል፣ ሀቀኛ እና በነባራዊ ሁኔታ ላይ የተመሠረተ ሪፖርት ለአፍሪካ ሕብረት ለማቅረብ ማቀዳቸውን ይፋ አድርገዋል።
ይህ ጉብኝት በዋናነት በአሁኑ ወቅት ከአባልነታቸው የታገዱት የሳሕል ሀገራት ከሕብረቱ ጋር ዳግም የሚገናኙበትን "የትብብር ድልድይ" ለመገንባትና ለማጠናከር ያለመ ነው። የቡሩንዲ ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት እንደገለጸው፣ ውይይቱ በቀጣናው ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚደረገው ጥረት አካል ነው።
የስፑትኒክ ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ ይህ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ በቡርኪና ፋሶ እና በጎረቤቶቿ ላይ የሚታየውን ጫና ለማርገብ ትልቅ ፋይዳ ሊኖረው ይችላል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) #getutemesgen #getu
#አፍሪካ_ሕብረት #ቡርኪና_ፋሶ #ኢብራሂም_ትራኦሬ #ኤቫሪስቴ_ንዳይሺሚዬ #ሳሕል #አፍሪካ #ሰላም_እና_መረጋጋት

4 months ago
የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መንግሥት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲበተኑ ወሰነ
የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መንግሥት ሁሉም ፖለቲካዊ ፓርቲዎች እንዲበተኑ እና የሚተዳደሩበት ሕጋዊ ማዕቀፍ እንዲፈርስ ወሰነ።
ሐሙስ ዕለት ውሳኔውን ያስተላለፈው የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር የሚኒስትሮች ምክር ቤት መሆኑን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
በአውሮፓውያኑ መስከረም 2022 በመፈንቅለ መንግሥት ወደ ሥልጣን የመጣው የካፕቴይን ኢብራሒም ትራኦሬ አገዛዝ ሥልጣኑን ለማራዘም የተለያዩ መንገዶች እየተጠቀመ ነው የሚል ትችት ይቀርብበታል።
የቡርኪና ፋሶ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ኤሚል ዜርቦ ውሳኔው "ለሀገር መልሶ ግንባታ" የተላለፈ ነው በማለት ከዚህ ቀደም የነበረው መድብለ-ፓርቲ ሥርዓት ለብዝበዛ እና ለአሠራር ብልሹነት የተጋለጠ ነው ሲሉ መተቸታቸው ተሰምቷል።
ሚኒስትሩ አክለው በሀገሪቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው ለክፍፍል እና የማኅበረሰብ ጥምረት እንዲዳከም ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
ቡርኪና ፋሶ ከመፈንቅለ-መንግሥቱ በፊት ከ100 በላይ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የነበሯት ሲሆኑ 15 ፓርቲዎች በአውሮፓውያኑ 2020 ከተደረገው ምርጫ በኋላ ወደ ፓርላማ መግባት ችለው ነበር።
አዲሱ የመንግሥት ውሳኔ ሁሉም ፖለቲካዊ ፓርቲዎች እንዲፈርሱ ከማስገደዱም በተጨማሪ የተበተኑት ፓርቲዎች ንብረቶች ለመንግሥት ተላልፈው ይሰጣሉ።
የሳሕል ቀጣናዋ ሀገር እንደ ጎረቤቶቿ ማሊ እና ኒጀር ከአል ቃኢዳ ጋር ግንኙነት ያለውን ኢስላሚክ ስቴት ታጣቂ ቡድን ለማዳከም እየጣረች ትገኛለች። ታጣቂ ቡድኑ በአካባቢው በርካታ ሰዎችን ገድሏል፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉም ምክንያት ሆኗል።
BBC