Logo
YenetaTube
የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መንግሥት ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲበተኑ ወሰነ

የቡርኪና ፋሶ ወታደራዊ መንግሥት ሁሉም ፖለቲካዊ ፓርቲዎች እንዲበተኑ እና የሚተዳደሩበት ሕጋዊ ማዕቀፍ እንዲፈርስ ወሰነ።
ሐሙስ ዕለት ውሳኔውን ያስተላለፈው የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር የሚኒስትሮች ምክር ቤት መሆኑን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።
በአውሮፓውያኑ መስከረም 2022 በመፈንቅለ መንግሥት ወደ ሥልጣን የመጣው የካፕቴይን ኢብራሒም ትራኦሬ አገዛዝ ሥልጣኑን ለማራዘም የተለያዩ መንገዶች እየተጠቀመ ነው የሚል ትችት ይቀርብበታል።
የቡርኪና ፋሶ የሀገር ውስጥ ሚኒስትር ኤሚል ዜርቦ ውሳኔው "ለሀገር መልሶ ግንባታ" የተላለፈ ነው በማለት ከዚህ ቀደም የነበረው መድብለ-ፓርቲ ሥርዓት ለብዝበዛ እና ለአሠራር ብልሹነት የተጋለጠ ነው ሲሉ መተቸታቸው ተሰምቷል።
ሚኒስትሩ አክለው በሀገሪቱ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መኖራቸው ለክፍፍል እና የማኅበረሰብ ጥምረት እንዲዳከም ምክንያት ሆኗል ብለዋል።
ቡርኪና ፋሶ ከመፈንቅለ-መንግሥቱ በፊት ከ100 በላይ የተመዘገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የነበሯት ሲሆኑ 15 ፓርቲዎች በአውሮፓውያኑ 2020 ከተደረገው ምርጫ በኋላ ወደ ፓርላማ መግባት ችለው ነበር።

አዲሱ የመንግሥት ውሳኔ ሁሉም ፖለቲካዊ ፓርቲዎች እንዲፈርሱ ከማስገደዱም በተጨማሪ የተበተኑት ፓርቲዎች ንብረቶች ለመንግሥት ተላልፈው ይሰጣሉ።
የሳሕል ቀጣናዋ ሀገር እንደ ጎረቤቶቿ ማሊ እና ኒጀር ከአል ቃኢዳ ጋር ግንኙነት ያለውን ኢስላሚክ ስቴት ታጣቂ ቡድን ለማዳከም እየጣረች ትገኛለች። ታጣቂ ቡድኑ በአካባቢው በርካታ ሰዎችን ገድሏል፤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉም ምክንያት ሆኗል።

BBC

4 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.