4 days ago
#wallagauniversity
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ተቋሙን ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት ለማሸጋገር በሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፣ ተቋማዊ አቅም፣ የሰነድ ዝግጅት እና የሰው ኃይል ልማት ላይ ውይይት አካሒዷል።
ወደ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በመሔድ የተገኘ የቤንችማርኪንግ ተሞክሮ በመድረኩ ቀርቧል።
ዩኒቨርሲቲው ለራስ ገዝነት ሽግግር አስፈላጊ በሆኑ የዲጂታላይዜሽን፣ የውስጥ ገቢ አቅም ማጠናከር እና መሠል ሥራዎች ላይ በትኩረት መስራት እንዳለበት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተስፋዬ ለማ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
የሽግግር ሰነዶችና ፖሊሲዎች ማዘጋጀት፣ የራስ ገዝነት ጽ/ቤት ማቋቋም፣ የምርምርና የፋይናንስ አቅምን ማጠናከር እንዲሁም ተቋማዊ የሽግግር ካርታ ማዘጋጀት ቀጣይ ሥራዎች መሆናቸው በውይይቱ ተጠቁሟል።
@tikvahuniversity

8 days ago
#wallagauniversity
ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በትምህርት ሚኒስቴር የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የፕሬዝዳንቶች አሰያየም መመሪያ ቁጥር 1146/2018 መሰረት ፕሬዝዳንት እና ሁለት ምክትል ፕሬዝዳንቶችን አወዳድሮ ለመመደብ አመልካቾችን በመመዝገብ ላይ ይገኛል፡፡
ለውድድር ክፍት የሆኑ የአመራርነት ሥራ መደቦች፦
➻ ፕሬዝዳንት
➻ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት
➻ የምርምርና ማኅበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዝዳንት
የተቀመጡ ዝርዝር መስፈርቶችን የሚያሟሉ አመልካቾች ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ከመንግሥታዊ ተቋማት እንዲሁም መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ልምድ ያላቸው አመልካቾች መወዳደር ይችላሉ ተብሏል፡፡
በሥራ ቀናት በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ስራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁ. 116 ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርባችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
(ዝርዝር ማስታወቂው ከላይ ተያይዟል፡፡)

Comments