Logo
Getu Temesgen
የፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ሚስት "ሴት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ" ለፍርድ ቤት ሊያቀርቡ መሆኑ ተሰማ
#ethiopia | የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባሳለፍነው ግንቦት ወር ለጉብኝት ወደ ደቡብ ምስራቅ እስያዊቱ ቬትናም ዋና ከተማ ሃኖይ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሰው ከአውሮፕላን ሊወርዱ ሲሉ የባለቤታቸውን ቀዳማዊት እመቤት ብሪጄት ማክሮን "ጥፊ ሲቀምሱ" በካሜራ ዕይታ ውስጥ ከገቡ ወዲህ በርካታ የሴራ ተንታኞች "የማክሮን ሚስት ዓለም ያወቀውን የአገር መሪ በአደባባይ የሚደበድቡት ወንድ ቢሆኑ ነው ፤ ፊታቸውም የሚያሳብቀው ይሄንኑ ነው" በማለት ውንጀላ ማቅረብ መጀመራቸውን ተከትሎ ፕሬዝዳንቱ እና ባለቤታቸው የስም ማጥፋት ክስ መስርተው ጉዳዩ በዓለም ዙሪያ መነጋገሪያ ሆኖ ቆይቷል።

ይሁንና ክሱ የተመሠረተው በአሜሪካ በመሆኑ ፤ በአገሪቱ ሕግ መሠረት በታዋቂ ሰዎች ላይ የስም ማጥፋት ተፈጽሟል የሚል ውንጀላ ሲቀርብ ከሳሽ ወገን ተከሳሹ "ሆን ብሎ ጉዳት ለማድረስ ሐሰተኛ መረጃ ማሰራጨቱን" ማረጋገጥ የሚጠበቅበት ሲሆን ይህንን ተከትሎም የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን ባለቤታቸው ብሪጄት ማክሮን ፣ ሴት መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ፎቶግራፍ እና ሳይንሳዊ ማስረጃ ለአሜሪካ ፍርድ ቤት ሊያቀርቡ መሆኑ ተሰምቷል።

ከቢቢሲ ፌም አንደር ፋየር ፖድካስት ጋር ቆይታ ያደረጉት የቀዳማዊት እመቤት ብሪጄት ማክሮን ጠበቃ ቶም ክሌር ፣ ይህ የስም ማጥፋት ዘመቻ "በከፍተኛ ሁኔታ የሚያበሳጭ" እና በፕሬዝዳንቱ ላይም ተጽዕኖ ያሳደረ ነው ብለው ቀዳማዊት እመቤቷ እርጉዝ ሳሉ እና ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ጨምሮ ሌሎች ሳይንሳዊ ማስረጃዎችን ለፍርድ ቤቱ አቅርበን በሐሰት የጠፋው ስማችንን ለማደስ ቆርጠን ተነስተናል ሲሉ ተናግረዋል።

በቃልኪዳን ይጥና #artstv

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.