Logo
YenetaTube
‎ በሊቢያ አቅራቢያ ዛሬም የስደተኞች ህይወት አለፈ!

‎የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ሰላምና ከጦርነት ለማምለጥ ከአፍሪካ ወደ አውሮጳ በመሻገር በጉዞ ላይ የነበረ የስደተኞች መርከብ በሊቢያ አቅራቢያ ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ቢያንስ 50 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ ።

‎ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ማክሰኞ እንዳስታወቀው በእሁድ እለት 75 ሱዳናውያን ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች መርከብ በሊቢያ የባህር ዳርቻ በተቃጠለች ሲሆን በአደጋው ቢያንስ 50 ሰዎች መሞታቸውን ቀሪዎቹን በህይወት የተረፉ 24 ሰዎች የህክምና ድጋፍ ማድረጉን ገልጿል።

‎"ወደ ዉጭ ለመሄድ በደህና እና ህጋዊ መንገዶች የሚያገኙት በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ ስለሆነ በተለይም በምስራቅ አፍሪካ በህገዉጥ መንገድ ጉዞ ብቸኛው አማራጭ ተደርጓል ያለዉ ተቋሙ እነዚህን አደገኛ ጉዞዎች ለማስቀረት እውነተኛው መፍትሄ በሱዳን ያለውን ጦርነት ማቆም ነው ሲል ተናግሯል ።

‎በሱዳን በጦር ኃይሉ እና በወታደራዊ ሃይሎች መካከል ያለው ጦርነት ባለፉት ሁለት አመታት ከ140,000 በላይ ስደተኞችን ወደ በሊቢያ በኩል እንዲሰደዱ ማድረጉን የገለፀዉ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኤጀንሲ ከአሁኑ አደጋ በተጨማሪ ከጥር 1 እስከ መስከረም 13 ባለው ጊዜ ውስጥ በማዕከላዊ ሜዲትራኒያን መንገድ ላይ ቢያንስ 456 ሰዎች ሲሞቱ 420 ጠፍተዋል ሲል አይኦኤም ገልጿል።

‎በነሀሴ ወር ሁለት ጀልባዎች በደቡባዊ ኢጣሊያ ደሴት ላምፔዱዛ መስጠማቸዉን በወቅቱ ቢያንስ 27 መሞታቸውን በተመሳሳይ በሰኔ ወር ቢያንስ 60 ስደተኞች እና ፍልሰተኞች በሊቢያ የባህር ዳርቻ ሁለት መርከብ ባህር ውስጥ ሰጥመዋል አብዛኞቹ ስደተኞችም ሱዳናዊ ኢትዮጵያዊ ኤርትራውያን ናቸዉ። ብሏል ።

‎በ2011 የሊቢያ መሪ ሙአመር ጋዳፊ ከወደቁ ወዲህ ወደ 867,055 የሚጠጉ ስደተኞች መኖሪያ የሆነችው ሊቢያ ለስደተኞች ወይም ወደ አውሮፓ ለመግባት ለሚሞክሩ ስደተኞች መሸጋገሪያ መስመር ሆናለች።ያለዉ ኢጀንሲዉ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እና የተባበሩት መንግስታት ኤጀንሲዎች በሊቢያ ውስጥ በስደተኞች እና በስደተኞች ላይ ስልታዊ በደል፣ ማሰቃየትን፣ አስገድዶ መድፈርን እና ዝርፊያን ጨምሮ መዝግበዋል። ሲል አሳዉቋል ሲሉ አልጀዚራን ጨምሮ አለምአቀፋዊ ሚዲያዎች አስነብበዋል ።

‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ




11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.