ውይይይ ሬዲዮ እኮ! የልቤና ሱሴም ነው! "ያለሽቦ ቃል ሚያሳልፍ የንፋስ ስልክ የተባለው 'ሬዲዮ'-የኢትዮጵያው 90ኛ የልደት ሻማውን ለኮሰ።
#ethiopia | መስከረም 2/1928 ዓ.ም ግርማዊ ጃንሆይ ለመጀመሪያ ጊዜ በሬዲዮ ስርጭቱ ንግግር አደረጉ፤ ልዕልት ጸሐይ በእንግሊዝኛ መልዕክት አስተላልፈውበታል፤ ኢጣሊያም ኢትዮጵያን ልትወር ያንዣበበችበት ዋዜማ ነበር።
ሬዲዮው በ9 ሀገራዊና በ3 የውጭ ቋንቋዎች ዜናና ፕሮግራሞችን እንደሚያስተላልፍ ያመሳከርኩት የታሪክ ሰነድ ያመለክታል።
በሞያ ብቃት የተገራሁበትን የድሮ ቤቴን ዛሬም ቢሆን በአፍሪካ ብዙዎች ከኋላው ተፈጥረው ቢቀድሙትም ከነጉድለቶቹ እወደዋለሁ።
ዋናው የኢትዮጵያ የሕዝብ ሀብት ነው ፥ ሲቀጥል ፈር ቀዳጁ የሀገር ልጆች የመሰረቱት አፍሪካዊ ሚዲያ መሆኑ እና ከሕዝብ ጋር ተሳስሮ ክፉና ደጉን እየተጋራ የዘለቀም ስለሆነ።
የኢጣሊያ አንሶልዶ ኩባንያ በሰራው የንፋስ ስልክ ጣቢያ ስርጭት የጀመረው ሬዲዮ እስከ1956 ዓ.ም ድረስ በአጭር ሞገድ ማሰራጨቱ ፉጨትና ጩኸት ስለሚቀላቀልበት በጥራት አይሰማም ነበር።
ሬዲዮን ጨምሮ ቴሌቪዥንና ጋዜጣ ያኔ ድሮ ዋነኞቹ የመረጃ ምንጮች (mainstream media)፥ ቀጥሎ የተለመዱ የዜና አገልግሎት መስጫዎች (traditional media) ሲባል ቆየና ከ10 አመት ወዲህ ስያሜው በውርስ መገናኛ ብዙኀንነት (በ-legacy media) ይጠራሉ።
ቀደምቱ ሚዲያ ፈተና ተጋርጦባቸው እየተንገዳገዱ ነው። የታዳሚያን በሩጫ በተሞላ አኗኗራቸው ሳቢያ ቤት ቁጭ ብለው ሚዲያ የመጠበቅ ዝንባሌ ከመቅረቱ ጋር የተያያዘው የባህሪ ለውጥ መምጣቱ (Shift in audience behaviour) አንዱ ነው።
ፈጣን የዲጂታል ቴክኖሎጂው እንቅስቃሴን የዋጁ መረጃን በፈለጉት ጊዜና ቦታ እጅ መዳፍ ላይ
ማምጣቱ (Swift changes in technology) ሌላው በጥንቶቹ ሚዲያ ላይ የተደቀነ ፈተና ነው።
በተጨማሪም የገበያ ውድድሩ አቅጣጫ ከፍጥነት፥ ተደራሽነት፥ ዋጋ፥ ጥራትና አዋጭነት አኳያ በአማራጭ ብዛት ትኩረቱ መለወጡ (Shift in Market competition) አስተማማኝ ዘላቂ ገቢን ለማረጋገጥ እየተፈተኑ ነው።
እናም የዲጂታል ቴክኖሎጂው ፈጣን ለውጥ -"If you can't change, the change will change you" - ወቅቱን በሚዋጅ መልኩ ካልተለወጥክ - ለውጡ ራሱ ይለውጥሃል ነው ቅኔው።
እናም ውድድሩ ትንቅንቅ በሆነበት ዘመን የዕድሜ ረዥምነት ላይ ብዙ ከመመፃደቅ ያለፈ ፋይዳው የቀጠለ (Relevant) እና የገቢ አዋጭነቱ አዝላቂ (Viable) የሆነ ተጨባጭ ስራን መስራት ይጠይቃል።
እናም የአናሎግ ዘመኖቹ የሕትመትና የብሮድካስት ሚዲያዎች በቴክኖሎጂ የዝማኔ ለውጥ ከመጡት የዲጂታልና የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲሁም ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር የተዋጁ አሰራሮች ጋር አጣጥሞ የማስኬድ ስልትን መከተል የግድ ይላቸዋል፤አሰራሩም Media convergence strategy በሚል ይጠራል።
ሬዲዮ ለሚለው ቃል ወካይ አማርኛ ሲሰጠው - "ያለሽቦ ቃል የሚያሳልፍ መኪና" ተብሎ ተተርጉሟል።
የመሰረት ድንጋይ በተቀመጠበት ቦታ የተጻፈ-'በንፋስ የሚሄድ ስልክ' የሚል ነበርና ዛሬ አካባቢውም 'ንፋስ ስልክ' የሚል መጠሪያውን ይዞ ቀረ።
በኢትዮጵያ ሬዲዮ-ዜና ፋይል፥የሰሞኑ ታላቅ ዜናና ዓለም በዚህ ሳምንት እጅግ ተወዳጅ ከነበሩት የዜናና መዋዕለ ዜና መካከል ይጠቀሳሉ።
ከፕሮግራሞች መካከል "የእሁድ ጠዋት" ፥ "የቅዳሜ ከሰአት መዝናኛ" ፥ "ኢትዮጵያን እንቃኛት"፥ "የኪነ - ጥበባት ምሽት"፥ "ከመድሀፍት ዓለም"፥"ከአድማስ ባሻገር"፥ "አውደ ገጠር" እና "ኢኮኖሚያችን" ጥቂቶቹ ናቸው።
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሲመሰረት ሂደቱን የቀረጸው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ነው፤ የመሪዎቹ ንግግሮች የታሪካዊ ሁነት (Historical events Speech) ተብሎ በኢትዮጵያ ሬዲዮ የድምፅ ማህደር ተሰድሮ ይገኛል።
የጥበቡ ሰውና የሸገር ሬዲዮ አንዱ መስራች ተፈሪ አለሙ፥ ከያኒውና የኢትዮ ኤፍ.ኤም ሬዲዮ አንዱ መስራች ሰራዊት ፍቅሬ እና ጋዜጠኛ መሳይ አለማየሁ ታሪክን ከትናንት፥ ዛሬና መጪውንም አክለን ተወያየን።
የእናትፋንታ ውቤ ውይይቱን ስትመራ መሳይዬ የድሮ የስቱዲዮ ማጋፈሩ ታውሶት እንደ እኛ እንግዳ ብቻ አልነበረም።
ቀዳማዊ አፄ ኃ/ሥላሴ ሐምሌ 14/ 1923 ዓ.ም በነፋስ ስልክ ለሬዲዮ ጣቢያ መቋቋም የመሰረት ድንጋይ አኖሩ፤ ጣቢያው ተመርቆ አገልግሎት የጀመረው ግን በ1927 ዓ.ም ነው።
ስርጭቱ ኢትዮጵያን እንዲሸፍን ተጠንቶ በ9 ከተሞች የሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያ ቢሰራ ተብሎ ታቀደ - በ1956 ዓ.ም።
ይሁንና የአካባቢ ሽፍታ በቀላል መሳሪያ ጣቢያውን ተቆጣጥሮ "ንጉሥ ሆኛለሁ" ቢል ችግር ይፈጥራል ተባለ።
ስለዚህ ጣቢያዎቹ አ/አ፥ ሐረር እና አስመራ ላይ ብቻ ተቋቁመዋል።
ስርጭቱ ርቆ ስለማይወጣም የአዲስ አበባው ሬዲዮ በሚል ይተረብ ነበር።
የትራንስሚተር ድክመቱ ፍሪኩዌንሲ እንዳይረጋ ሆኖ ሞያተኛውንም ለፍቶ መና ሲያደርገው ቆይቷል።
በ1959ዓ.ም ግን ቀ/ኃ/ሥላሴ 35ኛ የዘውድ በአላቸው ወቅት የሚዲየም ዌቭ ማሰራጫ መርቀው ከፈቱ።
አዲሱን የማሰራጫና መቅረጫ መሣሪያዎች ተጠቅሞ በምዕራብ አፍሪካና ለምዕራብ አውሮፖ በእንግሊዝኛና ፈረንሣይኛ፤ ለምስራቅና መካከለኛው እስያ በአረብኛ፤ እንዲሁም ለመካከለኛው እና ለምስራቅ አፍሪካ በስዋህሊ ቋንቋዎች ፕሮግራሞችን በማስተላለፍ የተደራሽነቱን አድማስ አሰፋ።
እናም ይህ ከአፍሪካም አልፎ አለም አቀፍ ሚዲያ ለመሆን አልሞ ብዙ ርቀት የተጓዘው በነፃዪቱ ኢትዮጵያ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሬድዮ ዛሬ ከዕድሜ ቆጠራ በዘለቀ ይህን ራዕይ የት አደረሰው?
የሬዲዮ ቴክኒክ ክፍሉም በቴሌ ስር ስለነበር - አብዛኞቹን ማስተላለፊያና ማሰራጫ መሳሪያዎችን የመትከልና መጠገን አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው በቴሌኮምዩኒኬሽን መ/ቤት ነበር።
እሸቱ ገለቲ

9 months ago