Logo
FIDEL POST NEWS
በአዲስ አበባ በአዲስ ዓመት ባልና ሚስት በከሰል ጭስ ታፍነው መሞታቸው ተነገረ

በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ አመት ዋዜማ እና በእለቱ በትራፊክም አደጋ የሞተሰው አለመኖሩን እና የወንጀል አደጋ አለመድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ የተናገሩ ሲሆን ከወንጀል ውጭ በከሰል ጭስ መታፈን የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን ገልፀዋል።

በለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7ጣፎ ኮዲሚኒየም እድሜቸው 75 አመት አዛውንት ጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አመት ዋዜማ ምሽት በከሰል ጭስ ታፍነው ህይወታቸው አልፏል። በተመሳሳይ  በለሚኩራ ክፍለከተማ ወረዳ 13 ህዳሴ ትምህርት ቤት ጀርባ በአዲስ አመት መስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም ምሽት 6 ሰአት ባለትዳሮች በከሰል ጭስ ታፍነው ሞተው መገኘታቸውን ኮማንደር ማርቆስ ተናግረዋል።

ባለትዳሮቹ እሱ የ35 አመት ወጣት የትዳር አጋሩም ደግሞ የ27 አመት ወጣት መሆናን ፖሊስ የገለፀ ሲሆን  በከሰል ጭሱ ሁለቱም ሞተው መገኘታቸውን ተነግሯል።
11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.