Logo
FastMereja
በብዙ ውጥንቅጥ ልብ ሰባሪ ኹነቶች መሐል አሳልፎ፤ ይሄን ቀን ያሳየን፣ ዘመን ለንስሐ የጨመረልን የዘመናት ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው🙏

ዘመን ለምስጋና!
በሀገር ውስጥና በመላው አለም የምትገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንኳን ለ 2018 ዓ. ም. ( ዘመነ ማርቆስ ) በጤና አደረሰን አደረሳችሁ።

አሮጌውን ዘመን አሳልፎ አዲስ ብለን እንድንጠራ ያስቻለን፤ በብዙ ውጥንቅጥ ልብ ሰባሪ ኹነቶች መሐል አሳልፎ፤ ይሄን ቀን ያሳየን፣ ዘመን ለንስሐ የጨመረልን የዘመናት ባለቤት ልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይድረሰው🙏

አዲስ ዓመት፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ጅማሬ።
ክረምት አልፎ መስከረም ሲጠባ፣ ምድር በአደይ አበባ አጊጣ ፣ ጭጋጋማው ሰማይ በፀሐይ ሲፈካ፣ አዲስ ዝማሬ፣ አዲስ ዜማ መንፈስን ያድሳል።

የቡሄው ዜማ በ'አበባ አየሽ ወይ' ሲተካ የወቅቶች መቀያየር፣ የተፈጥሮ ፍሰት፣ እድሜ ሰጥቶት ላስተዋለ ምንኛ ድንቅ ነው!

በሙላት በጉድለት፣ በሀዘን በደስታ፣ በሀሴት በስብራት፣ በቁጣ በሳቅ፣ በጭንቀት በእረፍት፣ በመዛል በብርታት፣ በሚፈራረቁ ስሜቶች ሆነን የሚፈራረቅ ወቅትን፣ ዓመትን ማየት በቸርነቱ ነው።

"በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ፥ ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል።"
መዝ ፷፭:፲፩

መጪውን ዘመን ይባርክልን!
ክፉውን ከሀገራችን ያርቅልን!
ያዘኑ የሚፅናኑበት፣ የታመሙ የሚድኑበት፣ የሰላም ንፋስ የሚነፍስበት፣ እንቆቅልሻችን የሚፈታበት፣
የጤና፣ የሰላም፣ የፍቅር፣ የሀሴት ዓመት ይሁንልን!

መሠረት መብራቴ።
መስከረም 1, 2018 ዓ. ም.

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.