Logo
Getu Temesgen
#ልባዊ_ምስጋና
#ethiopia | የብሔራዊ ኩራት ተቃራኒው፣ ብሔራዊ እፍረት/ውርደት/ ነው። ይሄን ውረደት ደግሞ በየደረጃው ስለምንካፈለው “የወል ሸክም” ይሆናል። ይሄውም በጦር ሽንፈት፣ በኢኮኖሚ ድቀት፣ በሞራል ውድቀት፣ በገናኖች ሁለንተናዊ ጫና በመጉበጥ የሚያቀረቅሩበት እዳ ውጤት ነው” National or collective shame ።

የቅኝ ገዢዎችን ቀንበር በአባቶቻችን ተጋድሎ ያመለጥነው ቢሆንም፣ “ድህነት” የምትባል ክፉ ስያሜ ስታቆስለን ኖራለች። በሰለጠነው ዓለም የተጓዘ ኢትዮዽያዊ የሚለማመደው አንድ ሀቅ “ኃይለኞች ፍትህ/ርትእ እንዳለቸው” ነው። might is right እንደሚሉት መሆኑ ነው። የኢኮኖሚ የበላይነት የሚያስከትላቸው የድል ዝርዝሮች ለዚህ አጭር ጽሑፍ ስለማይጠቅመኝ እዚህ ላይ እገታዋለሁ።

ብሔራዊ ኩራት፣ ቀና ብሎ መሄድ እንደ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ያለ ገናን ተግባር መፈጸም ይጠይቃል። ሕዳሴን ብዙዎቻችን “ዳግማዊ አደዋ” ስንለው ቆይተናል። “እውነት ነው” ትልቅ ድል ነው። ይህ የድልና የተጋድሎ ታሪክ በሀገሩና በሀገሬው የነቃ ተሳትፎ የተገኘ ቢሆንም፣ የውስጥና የውጭ ጫናን ተቋቁሞ፣ በብዙ መከራ ለፍጻሜ ማድረስ ቆራጥና ሀገር ወዳድ መሪ ይጠይቃል። እኒህ ሰው ደግሞ ዶ/ር ዐቢይ ሆነዋል።

በግሌ፣ በዚህ ዘመን ቀና የምልበት ድልና እድል ስለሰጡኝ፣ ሀገሬ ጀምራ ከዳር የማድረስ ብቃት እንዳላት ስላሳዮኝ፣ ሌላ ደግሞ ሌላ ተሻጋሪ ተስፋ እንዳለ በተግባር ስለገለጡልኝ፣ በጥቅሉ የምካፈለው ብሔራዊ ምልክት ስለሰጡኝ፣ ለክቡር ጠቅላይ ምንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ልባዊ ምስጋናየን አቀርባለሁ። እውነትም ንጋት።
#አገኘሁ_አዳነ_ድልነሣሁ

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.