የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የ2024 ቢዋይዲ ሴጉል መኪና እና የባጃጅ እጣ አወጣጥ ስነስርዓት አካሄደ
👉አስማረ ቱፋ ከዓለምገና የ2024 ቢዋይዲ ሴጉል መኪና አሸናፊ ሆኗል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከነሐሴ 15 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የእንቁጣጣሽ ሎተሪን በዲጂታል ለገዙ ደንበኞች የተዘጋጀውን የBYD seagull 2024 ዘመናዊ መኪና እና የኤሌክትሪክ ባጃጅ የቦነስ ሽልማት ዕጣ ማውጣት ስነስርዓት አካሂዷል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት የእጣ አወጣጥ ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ያለም ተስፋንጋት፥ የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር እኩል በመራመድ ደንበኞቹን በየትኛውም ስፍራና በማናቸውም ጊዜ ሆነው የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በethiolottery.et እና በቴሌብር፣ በCBE BIRR እና በሌሎች አማራጮች ሎተሪን በዲጂታል መንገድ የሚገዙበት ልዩ አሰራር አመቻችተናል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ከታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽን ጋር በመተባበር የ2024 ቢዋይዲ ሴጉል መኪና እና የባጃጅ ሽልማት መስጠቱን የተቋሙ ም/ል ስራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ ታደሰ ተናግረዋል። ዕድል ከዲጂታል ዘመን ሲተዋወቅ፣ እድል ከቴክኖሎጂ ጋር ሲጣጣም ስጦታው እጅግ ዘመናዊና ዘመኑን የዋጀ ይሆናል ሲሉ አክለው ገልፀዋል።
የ1ኛ እጣ አሸናፊ የሎተሪ ቁጥር 3006063 ሲሆን የ2024 ቢዋይዲ ሴጉል መኪና አሸናፊ ሆኗል። አስማረ ቱፋ ከዓለምገና የቢዋይዲ ሴጉል መኪና አሸናፊ ሆኗል። የ2ኛ እጣ ዘመናዊ የኤሌክትሪ ባጃጅ መኪና አሸናፊ የሎተሪ ቁጥር 2482333 መሆኑን የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ይፋ አድርጓል። በተጨማሪም ኦሊያድ ደኑ ከሰበታ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ ባጃጅ ተሽከርካሪ አሸናፊ ሆኗል።
Seledadotio

11 months ago