ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ስራ ድርጅት በቅዱስ ዮሐንስ የዘመነ ክረምት ትምህርት መርሐ ግብር ያስተማራቸውን 368 ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
ሐመረ ብርሃን የብራና መጻሕፍት ሥራ ድርጅት ጅማሮውን የብራና መጻሕፍትን ማዘጋጀት ላይ በማድረግ ተነስቶ በአሁኑ ሠዓት ዘርፈ ብዙ የተግባረ እድ ሥራዎችን እየሰራ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡
ተቋሙ ከዚህ ጎን ለጎን “ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የዘመነ ክረምት አዳር የሕጻናት ትምህርት መርሐግብር" የሚል ማዕቀፍ በማዘጋጀት ሕጻናትን በክረምት የአዳር ቆይታቸው (summer camp) የተለያዩ የተግባረ እድ ትምህርቶችን ከአብነት ትምህርት፣ ከስነምግባር ትምህርት እና መሠረታዊ ከሆኑ የቤ/ክ ትምህርቶች ጋር አስተሳስሮ ያስተምራል፡፡
በዚህም ሕጻናት የአባቶችን ጥበብ ተረካቢ፣ ብሎም የሙያ ባለቤት እንዲሆኑ እና በዋናነት ዘላቂነት ባለው መንገድ መንፈሳዊ ተግባራትን እንዲተገብሩ ለማስቻል ይሰራል፡፡
በመሆኑም በ2ዐ17 ዓ.ም ባካሄደው የት/ት መርሐግብር ካለፉት ዓመታት በተሻለ አቅሙን በማሳደግ እድሜያቸው ከ7 እስከ 14 ዓመት ያሉ 368 ሕፃናትን ተቀብሎ በአዳሪና ተመላላሽ ተረክቦ አስተምሯል፡፡
ታዲያ እነዚህን ተማሪዎችንም ነሃሴ 25 በቦሌ መድሃኒያለም ካቴድራል ወላጆችና የክብር እንግዶች በተገኙበት በደማቁ አስመርቋል፡፡
በምርቃት መርሐግብሩ ላይ ደቀመዛሙርቱ ከመመረቃቸው በተጨማሪ የተማሪዎች የስዕልና የበገና አውደርዕይ የተደረገ ሲሆን በተጨማሪም የተለያዩ አጋር ድርጅቶች ምስጋና ቀርቦላቸዋል፡፡
ይህ በሐመረ ብርሃን የሚዘጋጀው የቅዱስ ዮሐንስ የዘመነ ክረምት የትምህርት መርሃ ግብር በየዓመቱ የሚካሄድ ሲሆን የዘንድሮው የ2017ቱ መርሐግብርም ለ5ኛ ጊዜ የተካሄደ ነው፡፡

10 months ago