Logo
YenetaTube
በቅን ልቦች አማካኝነት ቲክቶከሮቹ
በቁጥጥር ስር ውለዋል!

ማዳም ቤት ሆና ልጅቷ ራሷን ለማጥፋት ሙከራ አድራጋ ነበር::

አንድን የቲክቶክ ተጠቃሚ እና ተባባሪዋን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ። ተጠርጣሪዎቹ ከአዲስ አበባ ውጭ የምትኖርና ወደ ኢትዮጵያ ለዕረፍት የመጣችን ወጣት ሴት በቲክቶክ አማካኝነት አዲስ አበባ ተቀብለው

ወደ ጭፈራ ቤት ከወሰዷት በኋላ አጠጥተው በማስከር፣ እሷ ሳታውቅ ከእርሷ ጋር ያደረጉትን ምሽት በፎቶና በቪዲዮ ቀርፀው እንደያዙ ተገልጿል።

ወጣቷ ወደ ውጭ አገር ከተመለሰች በኋላ ቪዲዮና ፎቶዎችን በመላክ ገንዘብ እንድትሰጣቸው ሲያስገድዷት እንደነበርና ይህን ተከትሎም ወጣቷ በረኪና በመጠጣት ራሷን ለማጥፋት እንደሞከረች ዘገባዎች ያሳያሉ።

እንደደረሰን መረጃ ወጣቷ በጓደኞቿ ትብብር ከሞት ልትተርፍ ችላለች።

የለሚኩራ ፖሊስም ወጣቱ እና ተባባሪዋን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እየተደረገባቸው ነው።

ይህ አሳዛኝ ክስተት ወጣቶች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለሚፈጠሩ ተንኮሎች ትኩረት እንዲሰጡና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ማሳሰቢያ ነው።

እነዚህ ልጆች ከ600 ሺህ በላይ ተከታይ ያላችው ናቸው::

Via Gursha

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.