ማህበረሰብ ተኮር የመማር ማስተማር ስልቶችን የተከተለዉ ኩዊንስ ኮልጅ ከ4ሺበላይ ተማሪዎችን አስተምሮ አስመርቋል
ጥራት ያለዉን ሰፊ የትምህርት አማራጭ ለማህበረሰቡ ማቅረብ ብቁ ዜጎችን ማፍራትናፍላጎትን መሰረት ያደረገ ማህበረሰባዊ አገልግሎት መስጠትና ችግር ፈቺ የሆኑ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በማከናወን የሃገራችንን ማህበረሰባዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት በማሳለጥ የሚታወቀው ኩዊንስ ኮሌጅ ለ25ኛ ጊዜ ትናንት ነሀሴ 17/2017 ዓም.በአዲስአበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎቹን በድምቀት አስመርቋል።
ኩዊንስ ኮሌጅ ከ27 ዓመታት በላይ ማህበረሰቡን እያገለገለ የሚገኝ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ነዉ፡፡ ኮሌጁ በተለይም ከ10 ዓመት ወዲህ አገልግሎቱን ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ የካምፓስ ቁጥሩን በማሳደግ በቴክኒክና ሙያ የትምህርት ዘርፍ፣ በዲግሪ እንዲሁም በድህረ-ምረቃ ፕሮግራም በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በቀን፣ በማታ፣ እንዲሁም በርቀት የትምህርት መርሃ-ግብሮች በማስተማር ላይ ነዉ፡፡
ኩዊንስ ኮሌጅ በጥቅምት 1990 ዓ.ም (የዛሬ 27 አመት) በአዲስ አበባ ከተማ በአራዳ ክ/ከተማ በተለምዶ አጠራር አራት ኪሎ ግንፍሌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የቋንቋ ማሰልጠኛና የአጫጭር ስልጠናዎች መስጫ ተቋም ሆኖ ህጋዊ ፈቃድ በማዉጣት ነበር ስራዉን የጀመረዉ፡፡
ኩዊንስ ኮሌጅ በከተማችን በተለያዩ አካባቢ የሚኖረውን ማህበረሰብ በዝቅተኛ ክፍያ ተጠቃሚ በማድረግ እንዲሁም ገቢያቸው ዝቅተኛ ለሆኑና በተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት ለሚሰሩ ሰራተኞች/ የህብረተሰብ ክፍሎች/ የክፍያ ቅናሽ በማድለግ፤ ብሎም ሙሉ በሙሉ ነፃ የትምህርት ዕድል በማመቻቸት ህብረተሰቡን በሚገባ በማገልገል ላይ ይገኛል፡፡
ኩዊንስ ኮሌጅ በትናንትናው እለት በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም 2,614 ተመራቂዎች፤በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ደግሞ 1,582 በአጠቃላይ 4,196 ተማሪዎችን በዛሬው እለት(ነሐሴ 17/2017 ዓ.ም.)በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስድስት ኪሎ ካምፓስ ዋናው ጊቢ በሚገኘዉ ልደት አዳራሽ በድምቀት ሲያስመርቅ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶክተር ሞገስ ግርማ ለተመራቂዎች ልዩ መልዕክት አስተላፈዋል።
ኩዊንስ ኮሌጅ ዛሬ ያካሄደዉ የምርቃት ስነስርዓት በኮሌጁ ለ25ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ኮሌጁ በ4 ሰራተኞች ስራ የጀመረ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት ከ500 በላይ ቋሚና ኮንትራት ሰራተኞችን ቀጥሮ በማሰራት ላይ የሚገኝ ኮሌጅ ነዉ፡፡
ኮሌጁ ከተቋቋመ ጀምሮ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና፣ በዲግሪ እና በማስተርስ ፕሮግራም ከ50,000 በላይ ተማሪዎችን አስተምሮ አስመርቋል፡፡ወደፊትም ከወትሮው በተሻለ አኳኋን በክፍያ ቅናሽና ስፖንሰር በማድረግ የመማር ማስተማሩን ተግባራቱን አጠናክሮ ይቀጥላል።
እንደሚታወቀው ጌጅ ሰርቪስ ትሬዲንግ ሐውስ ፒኤልሲ በስሩ የሚተዳደሩ የትምህርት ተቋማት እና ሌሎች ያሉት ሲሆንጌጅ ሰርቪስ ትሬዲንግ ሐውስ በስሩ ከያዛቸው ተቋማት መካከል:- ጌጅ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ፣ ኩዊንስ ኮሌጅ፣ ሶፍትኔት የሥልጠና ማዕከል፣ ኤል ኤም ኢንተርናሽናል ሆቴል ስኩል፣ ግሬስ ኮሌጅ፣ ጌጅ አካዳሚ፣ ኤምጂኬ(MGK printing enterprise )AGET (African Global education & Technology )፣ AIHD (African international humanitarian development )፣ (ኤስኤምኤስትሬዲንግ )SMS trading plc የሚባሉ ተቋማት እንዳሉና ለበርካታ ዜጎች የትምህርት አገልግሎት ሲሰጡ እንደቆየ አሁንም በመስጠት ላይ ያሉ መሆናቸዉ የሚዘነጋ አይደለም።

12 months ago