Logo
YenetaTube
“ የአይ ኤስ አይ ኤስ አባላት ለጠቆመኝ 10 ሚሊዮን ዶላር እሸልማለሁ ” !/ አሜሪካ/

‎ አሜሪካ በአፍጋኒስታን የተመሰረተውና በሶማሊያ የሚገኘውን የአይ ኤስ አይ ኤስ የፋይናንስ ኦፕሬሽን ክንፍ በተመለከተ መረጃ ለሚሰጥ ማንኛውም ሰው የ10 ሚሊየን ዶላር ሽልማት እንደምሰጥ እወቁልኝ ማለቷ ተሰማ።

‎አሜሪካ ቡድኑ በማጭበርበር ፣ በመዝረፍ እንደዚሁም
‎በአገር ውስጥ በሚደረጉ ልገሳዎች፣ ታክስ፣ የአካባቢውን ሕዝብ እና የንግድ ድርጅቶች ዝርፊያ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር እና ህገ ወጥ የአሳ ማስገር ተግባራት ትርፍ እያገኘ ቀጠናዉን እያመሰሰ ነው ስትል ከሳለች ።

‎በመሆኑም ይህን ዋና መቀመጫውን ምስራቅ አፍሪካ ሶማሊያ ያደረገ ቡድን የገንዘብ እና ቁሳቁሶች ዝውውሮች አንቀሳቃሾች ለጋሾች ወይም የገንዘብ አመቻቾች ግብይቶችን የሚያመቻቹ የፋይናንስ ተቋማት ወይም የመለዋወጫ ቤቶች እንዲሁም የፋይናንስ ክንፍን አስመልክቶ መረጃን ለሚሰጣት ግለሰብም ሆነ ተቋም ሽልማት እንደምትሰጥ ነው ገልፃለች።

‎አሜሪካ እንደገለፀችው ከሆነ ISIS-K በትምህርት ቤቶች፣ በመስጊዶች፣ በሕክምና ተቋማት እና በቀብር ሥነ ሥርዓቶች ላይ በተፈፀመ ጥቃት በመቶ የሚቆጠሩ አፍጋኒስታውያንን ህይወት ጨርሷል።

‎ እ.ኤ.አ በግንቦት 2020 በካቡል የእናቶች ሆስፒታል 24 ሰዎችን ለገደለው ጥቃት ሃላፊነቱን ወስዷል፣። እ.ኤ.አ. በነሀሴ 2021 ISIS-K በካቡል አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዩናይትድ ስቴትስ ከአፍጋኒስታን በወጣችበት ወቅት 13 የአሜሪካ አገልግሎት አባላትን ለገደለው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ሃላፊነቱን ወስዷል።
‎በሴፕቴምበር 2022፣ ISIS-K በካቡል የሺአ ሰፈር በሚገኝ ኮሌጅ ውስጥ 19 ታዳጊዎችን ለገደለው የቦምብ ፍንዳታ ሃላፊነቱን ወስዷል።
‎እ.ኤ.አ ጃንዋሪ 3፣ 2024 ISIS-K ሁለት ፈንጂዎችን በማፈንዳት 100 ሰዎችን የገደለ እና ከ250 በላይ የሚሆኑ ሰዎችን በከርማን፣ ኢራን አቁስሏል። ISIS-K በሞስኮ አቅራቢያ በሚገኘው ክሮከስ ከተማ አዳራሽ የሙዚቃ ቦታ ላይ በማርች 2024 ቢያንስ 137 ሰዎችን የገደለ ጥቃት ፈጽሟል።

‎በጃንዋሪ 14፣ 2016 የዩኤስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ISIS-K በተሻሻለው የኢሚግሬሽን እና ዜግነት ህግ አንቀጽ 219 መሰረት የውጭ አሸባሪ ድርጅት አድርጎ ሰይሟል። ያለችው አሜሪካ ለጠቆማት ማንኛውም ግለሰብ አስር ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት እንደተዘጋጀች ያስነበበው አፍሪካን ቢዝነስ ኢንሳይደር ነዉ ።

‎የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ


10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.