ማን ሊያሸንፍ ይችላል?
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በ2018 በ20 ክለቦች መካከል እንደሚካሄድ ይታወል። አነጋጋሪው ነገር መቼ ይጀመራል? የሚለው ነገር ነው።
ባለኝ መረጃ መሰረት ሊግ ካምፓኒው ውድድሩን በመስከረም መጨረሻ ወይም በጥቅምት መጀመሪያ ለማስጀመር አስቧል።
የስርጭቱስ ጉዳይ?
DSTV ከሊግ ካምፓኒው ጋር የነበረውን የ5 ዓመት ኮንትራት ጨርሶ ወጥቷል። ስለዚህ በቀጣዩ ዓመት ሊጉ የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ይኖረዋል ወይስ አይኖረውም? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።
ባለኝ ተጨባጭ መረጃ መሰረት የቀጥታ ስርጭት ይኖረዋል። ይህንንም በተመለከተ ሊግ ካምፓኒው የዛሬ ወር ገደማ ባወጣው ጨረታ መሰረት አምስት የቴሌቪዥን ጣቢያዎች የጨረታ ሰነዱን ወስደዋል።
እነሱም፦ EBC፣ ፋና፣ OBN፣ አርትስ እና EBS ናቸው።
ሊግ ካምፓኒው የጨረታ ሰነዳቸውን እየመረመረ ሲሆን የ2018 የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግን የሚያስተላልፈው ቴሌቪዥን ጣቢያ በዚህ ሳምንት መጨረሻ ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።
እርሶስ ይሄንን የቀጥታ ስርጭት መብት ማን ሊያሸንፍ ይችላል ብለው ያስባሉ?
በጋዜጠኛ ምስጋናው ታደሰ

12 months ago