Logo
Getu Temesgen
ድምፃችን ይሰማ!
የረድኤት ተራድኦ ሠራተኞች
#ethiopia | እኛ የረድኤት ተራድኦ ድርጅት የነበርን ሰራተኞች የአሁኑን አሳሳቢ ሁኔታችንን ለማሳወቅ ይህንን ግልጽ ምክረ ሀሳብ እና ቅሬታ ያቀረብን ሲሆን ጉዳዩን ከዚህ እንደሚከተለው እናቀርባለን ።

በNovember 2024 ከአሜሪካ የትራምፕ አስተዳደር ከመጣ ጊዜ ጀምሮ፣ በአዲሱ የመንግስት ቅልጥፍና ዳይሬክቶሬት (Department of Government Efficiency) ትእዛዝ ሁሉም የእርዳታ እና የሕይወት አድን የእርዳታ ስራዎች በሙሉ ተቋርጦ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

በአሁኑ ጊዜ ከጥቂት የዘርፉ አስፈፃሚዎች በስተቀር አብዛኛዎቻችን ከስራ ተባረረን ወይም በእንጥልጥል(suspension )ላይ እንገኛለን ከእነዚህ ሠራተኞች መካከል IOM, Ocha, World Vision, CRS, IRC እና ሌሎችም ይገኙበታል ።

ቀደም ሲል እኛ እንደ ዶላር ገቢ ምንጭ (Hard Currency Source) ማግኛ ስለነበር ከተለያዩ ባንኮች የቤት እና መኪና ብድሮችን በአነስተኛ ወለድ ወስደን ነበር። ነገር ግን በተለይም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ የወለድ ተመን ማሻሻያ (Interest Rate Revision) ከማርች 7፣ 2025 ጀምሮ በቀጥታ ተግባራዊ አድርጓል። ይህ ለአብዛኛዎቻችን ከፍተኛ የኑሮ ጫና እና የፋይናንስ ችግር ፈጥሯል።

ባንኩ ሰራተኞቹ ያሉበትን አሁናዊ ሁኔታ ከግምት ያላስገባ ሲሆን፣ ምንም አይነት የእፎይታ ጊዜ አላስገኘልንም። በአሁኑ ጊዜ የሰራተኞቹ ቤተሰቦች ከፍተኛ የኑሮ ስጋት ውስጥ ይገኛሉ። በተለይም በባንክ የገዛንባቸው ንብረቶች ለሃራጅ ሽያጭ እየተጋለጡ ይገኛሉ ።

በዚህ ረገድ፣ የባንኩ አስተዳደር እና የቦርድ አመራሮች የቅሬታው ሰምተዉ ተገቢውን እርምጃ እንዲወስዱ በአክብሮት እንጠይቃለን።

የሚከተሉት እርምጃዎች አስፈላጊ ናቸው፦

1. የወለድ ተመን ማሻሻያውን እንደገና መገምገም
2. ለተበላሹ ብዱሮች ደንበኞች የእፎይታ ጊዜ መስጠት
3. የተበላሹ የብድር ክፍያ ዕቅዶችን ማዘጋጀት እንዲሁም
4. የመኪና ባለንብረቶች ኮድ 2 ወደ ኮድ 3 እንዲቀይር እና ሰርተን እንከከፍሉ ማመቻቸት የሚሉ የመፍትሔ ምክረ ሃሳቦችን እናቀርባለን።

በአክብሮት፣
የረድኤት ተራድኦ ሰራተኞች

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.