Logo
Getu Temesgen
የ28 ዓመቱ የአልጀዚራ ጋዜጠኛ አናስ ጀማል አልሸሪፍ ከትናንት በስቲያ እሁድ በጋዛ በተፈጸመ የእስራኤል የቦንብ ጥቃት ተገደለ።

የባያን ባለቤት : የሻምና የሳላህ አባት ላለፉት 22 ወራት ዓለምአቀፍ ጋዜጠኞች እንዳይገቡ በታገዱባት ጋዛ የህዝብ ድምጽ ሆኖ ብዙ ዋጋ ከፍሏል። በተደጋጋሚ ዛቻ እና የግድያ ሙከራ አስተናግዷል ። ከወራት በፊት ለእርሱ ጥቃት አባቱን አሳጥቶታል።

ወርሃ ጥር ብዙ ተስፋ የተደረገበት የተኩስ አቁም ስምምነት ሲደረስ በቀጥታ ስርጭት የአደጋ መከላከያ ሄልሜቱንና ልብሱን አውልቆ ደስታውን ገልጾ ነበር ። ስምምነቱም የአናስም ተስፋ የነበራቸው እድሜ ግን አጭር ነበር። ሁለት ወር ብቻ ።
..
እስራኤል የሃማስ ሰው ነው ብላ ትወነጅለዋለች። እሱና የሚያውቁት ብቻ ሳይሆኑ የተመድ ሰዎችም ከጋዛ ህዝብ ጋር እንጂ በፍጹም ከሃማስ ጋር ንክኪ የለውም ብለው መስክረውለታል ።
ከጋዛ ሰማይ ስር ሰላም ሰፍኖ : የሰው ልጆች ሰቆቃ አብቅቶ ወደትውልድ ቀዬው : ወደ ብላቴና ልጆቹ ወደ አስቃላን የመመለስ ተስፋ ነበረው ።
..
እንደ አላህ ፈቃድ እንጂ እርሱ ተስፋ እንዳደረገው አልሆነም። ከትናንት በስትያ 'ሚዲያ' የሚል ጽሁፍ ከተለጠፈበት የማረፊያ ድንኳኑ ደጃፍ ከሌሎች አራት ባልደረቦቹ ጋር ላይመለስ ሄደ።

ከሳምንት በፊት ስሞት አውጡልኝ ብሎ የኑዛዜ ቃሉን ጽፎ ነበር።

' ጋዛን እንዳትዘነጓት : እኔንም በጸሎታችሁ አስቡኝ' ብሏል ።
አላህ ይዘንለት
...

“I have lived through pain in all its details, tasted suffering and loss many times, yet I never once hesitated to convey the truth as it is, without distortion or falsification… If I die, I die steadfast upon my principles,” he wrote.

“Do not forget Gaza … and do not forget me in your sincere prayers for forgiveness and acceptance.”
..
May Allah forgive him !

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.