ቻይና ጠፈር ላይ ሆስፒታል ልትገነባ ነው‼️
በቻይና የሚገኙት የሼንዘን ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የሻንጋይ ኢንጂነሪንግ ማይክሮ ሳተላይቶች ማዕከል በቅርቡ በጠፈር ላይ ሆስፒታል በጋራ ለመገንባት የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።
ፕሮጀክቱ የጠፈርተኞችን ጤና ለማጎልበት እና በምህዋሩ ውስጥ የህክምና ክትትል ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።
የወደፊቱ የጠፈር ሆስፒታል በአይሮስፔስ፣ በህክምና እና በባዮሎጂ መስኮች ላይ እድገት በማስመዝገብ የጤና ድጋፍን በተመለከተ የላቀ ምርምር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
እንዲሁም ከጠፈር ተመራማሪዎች በተጨማሪ ወደ ጠፈር የሚጓዙ መደበኛ ሰዎችን ጤና ለመደገፍም ምርምር ያደርጋል ነው የተባለው።
እንደ ሲጂቲኤን ዘገባ በስምምነቱ መሰረት ሆስፒታሉን ለማቋቋም ሁለቱም ወገኖች በህክምና መሳሪያዎች፣ በፈጠራ የህክምና ቴክኖሎጂዎች እና በኤሮስፔስ ሳይንስ ላይ ተባብረው በመስራት ሆስፒታሉን እንደሚገነቡ ተገልጿል።
Seledadotio

1 year ago