Logo
YenetaTube
ለ ሁሉም የሚዲያ አካላት አዲስ አበባ

ጉዳዩ፦ ቅሬታን ማቅረብን ይመለከታል
ቀን 24/11/ 2017 ዓ.ም

ከላይ በርዕሱ እነደተጠቀሰው የፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽን ከ 3000 በላይ ስራ ፈላጊ ምሩቃንን በ 2017 ዓ.ም ለመቅጠር ለሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ኮታ ማከፋፈሉ ይታወቃል ። ይህን መሰረት በማድረግም በክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ያሉ የስራና ስልጠና ቢሮዎች ኮምሽኑ ባወጣው የመመልመያ መስፈርት መሠረት ከወረዳ እስከ ክልል የሁላችንም መረጃ በጥልቀት በማጥናትና በመመርመር ከ 1 እስከ 14 የተቀመጡትን መስፈርቶች ያሟላን ስራ ፈላጊ የመጀመሪያ እና ሁለተኛ ድግሪ ምሩቃንን ለፌደራል ጉምሩክ ኮሚሽን መለምለው መላካቸው ይታወቃል።

እኛም በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በኩል ምልመላውን አልፋቹሀል ለፈተና ብቻ ተዘጋጁ ተብለን ለ 1 ወር ያህል ስንዘጋጅ ከቆየን በኋላ በመጨረሻው ሰዓት የፈደራል ጉምሩክ ኮሚሽን እንደገና የወጣዉን የመመልመያ መስፈርት ባለጥበቀ ሁኔታ እነደተሰረዝን እና እንደማንካተት አሳውቆናል።

ኮሚሺኑ ብቁ አደላችሁም፤ አትካተቱም ያለን ስራ ፈላጊዎች፦

1, በሁለተኛ ዲግሪ በመደበኛው እና በኢመደበኛው መርሀ ግብር ከመንግስትና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተመረቅን እና እስካሁን ምንም አይነት ስራ ያልጀመርን፤
2, በመጀመሪያ ዲግሪ መኢመደበኛ መርሀ ግብር (extension, night, weekend, distance and summer) ከመንግስትና ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመርቀን እስካሁን ምንም አይነት ስራ ያልጀመርን፤
ነገር ግን በኮሚሺኑ ውሳኔ ብቁ አደላቹህም የተባልንበት ምክንያት እኛን ተመራቂ ስራ ፈላጊዎችን ሞራል የጎዳ፤ የመመልመያ መስፈርት ብሎ ያወጣቸዉን ነጥቦች ያልጠበቀ እና የጣሰ መሆኑ ታውቆ ይህ ጉዳይ እንደገና እንዲታይልን እና ትክክልኛ ውሳኔ እነዲስጠን በእናንተ በኩል የሚዲያ ሽፋን እነዲሰጥልን ስንል በትህትና እንጠይቃለን።

ከሰላምታ ጋር እጩ ተመልማይ ቅሬታ አቅራቢዎች

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.