አንቶኒ ኤግለር ይባላል በጡረታ የተገለለ የአሜሪካ ልዩ ሀይል አባል የነበረ ነው ።
አንቶኒ ከልዩ ሀይሉ በጡረታ ከተገለለ በኋላ ዩጂ ሶሉሽን በሚባል የግል ሴኪውሪቲ ካምፓኒ በኩል በአሜሪካና እስራኤል በሚመራው Gaza Humanitarian Foundation (GHF) ውስጥ የሚሰሩ አሜሪካውያንን ደህንነት ለመጠበቅ ወደጋዛ ሄዶ ለብዙ ወራት የቆየ ነው ።
እና ሰሞኑን ተመልሶ ወደ አሜሪካ ከሄደ በኋላ ከBBC ጋር ቃለ መጠይቅ ባደረገበት ወቅት እንዲህ አለ
..
" ይህ በምስሉ ላይ የምታዩት የአምስት አመት ልጅ ሲሆን ስሙ አሚር ይባላል ። አሚር ወደዚህ የእርዳታ መስጫ ጣቢያ የመጣው 12 ኪ/ሜትር ተጉዞ ነበር ። አንቶኒ ኤግለር በባዶ እግሩ ለሚሄደው በረሀብ የተጎሳቆለ ህጻን ትንሽ ሩዝ እና አንዳንድ ምግቦችን ሰጥቶት እንደጨረሰ ትንሹ አሚር እጁን ዘርግቶለት እየጨበጠው አመሰግናለሁ አለው ።
በዚህ ወቅት በህጻኑ ሁኔታ ልቡ የተነካው አንቶኒ ኤግለር አሚር ወዳለበት በመጠጋት በርከክ ብሎ ስለ እናንተ ግድ የሚላቸው ፡ ስለ እናንተ የሚያስቡ ሰወች አሉ አለው ፡ አሚር በርህራሄ የሚያወራውን አሜሪካዊ ኮለኔል ጭንቅላት በትናንሽ አቧራማ እጆቹ ይዞ ጥርት ባለ እንግሊዝኛ አመሰግናለሁ ካለው በኋላ የተሰጠውን ምግብ ይዞ ሄደ።
ከጥቂት ደቂቃ በኋላ የእስራኤል ጦር የእርዳታ ምግብ ሊወስዱ በመጡ የተራቡ ፍልስጤማውያን ላይ ተኩስ ከፈተ ።
በዚህ ተኩስ ብዙዎች በጥይት ተመቱ ፡ ከነዚህ መሀከልም ከደቂቃዎች በፊት በአቧራማ እጆቹ ጭንቅላቴን እየነካካ አመሰግናለሁ ያለኝ ትንሹ አሚር ይገኝበታል ።
አሚር በዚህ ተኩስ በጥይት ተመቶ ህይወቱ አልፋለች
ያየሁት ነገር ከምቋቋመው በላይ ሆነብኝ ፡ በዚህ ስፍራ በማየው አስፈሪ ነገር ምክንያት በስራ ላይ መቆየት የለብኝም በማለት ስራዬን ለቅቄ ወደ አሜሪካ ተመለስኩ ።
በጋዛ የዚህ አይነት እልቂት በየጊዜው ይከሰታል ፡ ይሄኔ የትንሹ አሚር ቤተሰብም በዚህ አይነት ሁኔታ ሞተው ምግብ ይዞ እንደሚመጣ አስባ የምትጠብቀው ትንሽ እህት ይኖረው ይሆናል በማለት የእስራኤል ጦር ፡ በተራቡና ፡ አንዳችም ጦር መሳሪያ ባልታጠቁ ፍልስጤማውያን ላይ የሚፈጽመውን በጭካኔ የተሞላ አስፈሪና ዘግናኝ ድርጊት አጋልጧል ።
( ፎቶው አሚር ከመ7ደሉ ከደቂቃዎች በፊት በአንቶኒ ኤግለር የተነሳ ነው )
Via: ዋስይሁን ተስፋዬ

1 year ago