" ዝናብን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው ወደሱ ፊትን አዙሮ በጸሎትና በምልጃ መለመን አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው "- ብፁዕነታቸው
📌በሰሜን ወሎ ዞን ለሚገኙ ምዕምናን ለ7 ቀናት የሚቆይ ፀለተ ምኅላ እንዲይዙ ታዘዋል።
የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደተናገሩት በዞኑ በተለይ ቆላማ በሆኑ ሁሉም በሚባሉ ወረዳዎች የዝናብ እጥረት በመከሰቱ ሰብል እንዳልተዘራና አርሶ አደሩም አዝኖ እንደተቀመጠ ገልፀዋል።
ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ምን አሉ ?
" ለወትሮው ከሚያዚያ ጀምሮ የሚዘሩ አዝርዕቶች ዘንድሮ በዝናብ እጥረት አዝርዕት አልተዘሩም ይባስ ብሎ በዚህ ክረምት የሚዘሩ እንደ ስንዴ፣ ገብስ፣ ባቄላ፣ አተርና ጤፍ የመሳሰሉት ተዘርተው በቅለው የሚታዩበት ጊዜ ነበር።
አሁን የሚታዩ ምንም አይነት ቡቃያ የለም። በተለይ በጉባላፍቶ፣ ሀብሩ፣ በራያ እና አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ መጋቢት አካባቢ ያለን ነው የሚመስለው ምንም አይነት ቅጠል የለም መሬቱ ደርቆ ነው ያለው።
ዝናብን የሚሰጥ እግዚአብሔር ነው ወደሱ ፊትን አዙሮ በጸሎትና በምልጃ መለመን አማራጭ የሌለው መፍትሄ በመሆኑ ከሀምሌ 21/2017 ዓ.ም ጀምሮ ኹሉም ገዳማት፣ አድባራትና አጥቢያ አብያተክርስቲያን በመገኘት ምዕምናን ለ7 ቀናት የሚቆይ ምኅላ ፀሎት እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፈናል " ሲሉ ገልፀዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቄት ወረዳ አደጋ መካላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ቅድመ ማስጠንቀቂያ ቡድን መሪ የሆኑትን አቶ አታለል አለሙን በዚሁ ጉዳይ አነጋግሯል።
በወረዳው ባሉ 34 ቀበሌዎች ውስጥ በ19ኙ ቆላማ ቀበሌዎች ከፍተኛ ዝናብ እጥረት መከሰቱን አቶ አታለል ተናግረዋል። ይህም በግብርና ስራው ላይ ጥላ አጥልቷል ነው ያሉት።
" በ15 ደጋማ ቀበሌዎችም አጥጋቢ ዝናብ እየዘነበ አይደለም እንዲህ አይነት ችግር ደግሞ ሰብሉ ቢበቅል እንኳን ተባይና የሰብል በሽታ እንዲከሰት ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥር ትልቅ ስጋት ፈጥሯል " ሲሉ ተናግረዋል።
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን በ11ዱ ወረዳዎች ከፍተኛ የዝናብ እጥረት መከሰቱን መረጃ እንዳላቸው የገለፁት አቶ አታለል ወትሮም ቢሆን አካባቢው የአፈር ለምነቱን ያጣ የምግብ ዋስትናውን ያላረጋገጠ ነው ብለዋል።
ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ለሰሜን ወሎ ዞን አደጋ መካላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ይመር አለሙ የእጅ ስልክ ላይ ደጋግመን ብንደውልም ስልኩ ባለመነሳቱ የተነሳ ሀሳብ አስተያየታቸውን ማካተት አልቻልንም ሲል የዘገበው ቲክቫህ ነው::

1 year ago