ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ቁጣቸውን አወጡ
📌ኦባማ በቁጥጥር ስር ሲውሉ የሚያሳይ በ AI የተፈጠረ ቪዲዮ አጋርተዋል ነው የተባለው
#ethiopia | የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻቸው ላይ ትኩረትን የሚስብ እና አነጋጋሪ የሆኑ ተከታታይ ልጥፎችን አጋርተዋል ተብሏል።
የትራምፕ የማህበራዊ ሚዲያ ቁጣ ከቱልሲ ጋባርድ ስለ ኦባማ አስተዳደር የ"ትራምፕ-ሩሲያ ትብብር" ታሪክን እንደፈጠረ የሚያሳዩ ሰነዶችን ከማጋራቷ ጀምሮ፣ የዴሞክራት ፖለቲከኞችን ብርቱካናማ ዩኒፎርም (የእስረኛ ልብስ) ለብሰው የሚያሳዩ ምስሎችን መልሶ እስከ ማጋራት ደርሷል ነው የተባለው።
በተለይ ትኩረትን የሳበው እና ውዝግብ የፈጠረው ልጥፍ ደግሞ በሰው ሰራሽ አድታውሎት(Artificial Intelligence - AI) የተፈጠረ ቪዲዮ ሲሆን፣ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በኦቫል ቢሮ ውስጥ በቁጥጥር ስር ሲውሉ የሚያሳይ ነበር ተብሏል።
የዚህ አይነቱ በ AI የተፈጠረ ይዘት መሰራጨት በፖለቲካዊ ዘመቻዎች ውስጥ የሐሰት መረጃ ስርጭት አሳሳቢነትን ዳግም አንስቷል ነው የተባለው።
ትራምፕ በእንቅስቃሴያቸው፣ ቀደም ሲል በኦባማ አስተዳደር ላይ የቀረቡ ክሶችን መልሰው በማንሳት እና የዴሞክራቲክ ፓርቲ ተፎካካሪዎቻቸውን በተለያዩ መንገዶች በመተቸት ላይ ይገኛሉ ነው የተባለው።
ይህ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴ በቀጣዩ የአሜሪካ ምርጫ ዙሪያ እየተካሄደ ያለውን የፖለቲካ ትኩሳት የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ባለሙያዎች እንደሚናገሩት፣ በ AI የተፈጠሩ የውሸት ምስሎች እና ቪዲዮዎች (deepfakes) የፖለቲካ ክርክሮችን ሊያዛቡ እና ህዝባዊ መተማመንን ሊያሳጡ የሚችሉ አደገኛ መሳሪያዎች ናቸው ተብሏል።
ይህ የትራምፕ ልጥፍ በዲጂታል ዘመን የሐሰት መረጃዎችን የመለየት አስፈላጊነትን እና በማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የሚደረጉ የይዘት ቁጥጥርን አስመልክቶ አዳዲስ ጥያቄዎችን ማስነሳቱ ተመላክቷል። #menahriafm

1 year ago