Logo
SeledaPost
የማዕድን እሰጥአገባ፣
የኦሮሚያ ማዕድን ባለስልጣን የሆንግኮንጉ ሺንግሹ ማዕድን እንዲያለማ የተሰጠው  ፍቃድ እንዲሰረዝ ጠየቀ

-  ሺንግሹ የወርቅ ፕሮጀክቱን አለመሸጡን አስተባብሏ፤ ግዢ የፈጸመው የአውስትራሊያው አስካሪ ዝምታን መርጧል

በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ላይ ሰፊ አንድምታ ባለው አኳኋን የኦሮሚያ ማዕድን ልማት ባለስልጣን (OMDA) የፌደራል መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን ማዕድን እንዲያለማ ሶስት ፈቃዶች የተሰጠው ሆንግኮንግ ዢንግሹ ማዕድን ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ኩባንያ (Hong Kong Xingxu Mining International Investment Co. Ltd) ፈቃዶቹ እንዲሰረዙ መጠየቁ ተገለጸ።

ባለስልጣኑ ለማዕድን ሚኒስቴር ሐምሌ ቀን 2017 ዓ.ም በጻፈው ደብዳቤ ሆንግ ኮንግ ሺንግሹ ኩባንያ የፌደራል እና የክልሉን መንግስት አዋጆች ባለማክበር፣ ስራውን ባግባቡ ባለማከናወን እና የአካሄድ ጥሰቶችን በመፈጸም “የገባውን ውል አላከበረምል” ሲል በመግለጽ የተሰጠው የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ እንዲሰረዝ ጠይቋል።

ባለስለጣኑ በተጨማሪም “በሆንግ ኮንግ ሺንግሹ ማዕድን ያገኘውን የታደሰ የማዕድን ፍለጋ ፈቃድ “እውቅና እንደማይሰጠው” አስታውቋል።

አስካሪ ሜታልስ የነጆ ወርቅ ፕሮጀክትን ሙሉ በሙሉ ጠቀለለው በሚል የቀረበውን መረጃ በተመለከተ አዲስ ስታንዳርድ ያነጋገራቸው የሆንግኮንጉ ኩባንያ ሺንግሹ ማዕድን የሀገር ውስጥ ስራ አስኪያጅ ሱራፌል ወንድማገኝ የመገናኛ ብዙሃኑ ዘገባዎች ትክክል አይደሉም ሲሉ አስተባብለዋል።

በአውስትራልያው አስካሪ ሜታልስ እና በሆንግ ኮንግ ሺንግሹ ማዕድን ኢንተርናሽናል ኢንቨስትመንት ኩባንያ መካከል የተደረገውን ስምምነት በተመለከተ እና አንድምታውን በተሻለ ለመረዳት አዲስ ስታንዳርድ ለአስካሪ ሜታልስ በይፋዊው የኢሜይል አድራሻ እንዲሁም በቀጥታ ለአስካሪ ሜታልስ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጂኖ ዲአና ጥያቄ ቢልክም ምላሽ አላገኘም። 

Seledadotio
Seledadotio
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.