ተለዋዋጭ እና ኢ-ተገማች በሆነ ዓለም አቀፋዊ የደኅንነት አውድ ውስጥ ሀገርን ማፅናት ያስቻሉ ስምሪቶች ተካሂደዋል - የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት
#ethiopia | ተለዋዋጭ እና ኢ-ተገማች በሆነ ዓለም አቀፋዊ የደኅንነት አውድ ውስጥ ሀገርን ማፅናት ያስቻሉ ስምሪቶች ማካሄዱን የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታወቀ።
የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጻም ሪፖርት እና የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አቅጣጫ ላይ ግምገማዊ ውይይት አካሂዷል።
የአገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ስትራቴጂክ አመራሮች በተገኙበት መድረክ በተካሄደው ውይይት በ2017 በጀት ዓመት ተለዋዋጭ እና ኢ-ተገማች በሆነ ዓለም አቀፋዊ እና ቀጣናዊ የደኅንነት አውድ ውስጥ ጫናዎችን በመቋቋም ሀገርን ማፅናት ያስቻሉ ስምሪቶች እና የኦፕሬሽን ሥራዎች መከናወናቸው ተጠቁሟል።
በበጀት ዓመቱ ተቋሙ የተሰጠውን መረጃ የመሰብሰብ እና የመተንተን ተልዕኮ ከመወጣት አንፃር ስትራቴጂክ፣ ኦፕሬሽናል እና ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ መረጃዎችን በማመንጨት ለውሳኔ ሰጪ አካላት ግብዓት እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።
የተሰበሰቡ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ ከሌሎች የፀጥታ እና መረጃ ተቋማት ጋር በመቀናጀት የሕግ የበላይነትን እና ተጠያቂነትን ማስፈን የሚያስችሉ የኦፕሬሽን ሥራዎች ተከናውነዋል።
በተለያዩ ሕገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች የተሳተፉ እና ከብሔራዊ ደኅንነት እና ጥቅም በተጻራሪ የተሰለፉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ መደረጉም ነው የተገለጸው። ይህን ተከትሎም አሁን ላይ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች የነበሩ የፀጥታ ችግሮች እየተፈቱ መሠረታዊ መሻሻሎች ታይተዋል።
በሀገሪቱ የተካሄዱ በርካታ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ጉባኤዎችን እንዲሁም የአቪዬሽን ደኅንነትን በማረጋገጥ ረገድ ምንም ዓይነት ክፍተት እንይፈጠር አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ውጤታማ ስምሪት ማካሄዱን አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አመልክቷል።
አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ የሥነ-ልቦና ጦርነትን ለመምራት እና ለማስተባበር በሕግ የተሰጠውን ኃላፊነት መሠረት አድርጎ ከውስጥ እና ከውጭ ሀገራችንን እና የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም እንዲሁም ብሔራዊ ደኅንነትን ዒላማ አድርገው የተቃጡ ጦርነቶችን የመመከት፣ የመከላከል እና አስፈላጊ ሲሆንም የማጥቃት እርምጃዎችን በመውሰድ ረገድ ስኬታማ ተግባር ማከናወኑ በመግለጫው ተጠቅሷል።
በበጀት ዓመቱ አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ባከናወናቸው ሥራዎች እንደ ተቋም መረጃን የመሰብሰብ፤ የመተንተን እና የመመዘን አቅምን ማሳደግ የተቻለበት፤ ብሔራዊ ጥቅምን ሊያስጠብቁ የሚያስችሉ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ስምሪቶች የተከናወኑበት፤ ቴክኖሎጂን መታጠቅ ብቻ ሳይሆን በራስ አቅም ማላመድ እና ማበልፀግ ላይ ውጤት የተገኘበት እንዲሁም ሀብትን አቀናጅቶ መጠቀም ልምድ የዳበረበት መሆኑ እንደ ጥንካሬ ተነሥቷል።
ባለፉት ዓመታት ትኩረት ተሰጥቷቸው በተከናወኑ የሪፎርም ሥራዎች በአሠራር ሥርዓት የዘመነ፤ የሰለጠነ የሰው ኃይል የያዘና ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂ የታጠቀ እንዲሁም ኢትዮጵያን የሚመስል ተቋም ለመገንባት የተደረገው ጥረት ውጤት የተገኘበት እንደነበር ተገምግሟል።
የመረጃ እና ደኅንነት ስምሪት ከተለዋዋጭ ሁኔታዎች ጋር ተጣጥሞ መካሄድ ስላለበት በቀጣይ የሪፎርም አጀንዳዎችን መከለስ እና ወቅቱን የሚዋጁ አዳዲስ አቅጣጫዎችን መስቀመጥ እንደሚገባ በውይይት በመድረኩ ተጠቁሟል።
በሚቀጥለው ዓመትም የሀገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ሙሉ ለሙሉ ወደ ተሟላ ሰላም እና መረጋጋት መለወጥ፤ ለሀገራዊ ምርጫ ምቹ መደላድልን መፍጠር፤ ተለዋዋጭ ለሆኑ ሁኔታዎች ስትራቴጂካዊ ዝግጁነትን ማጠናከር ዋናዎቹ የትኩረት አቅጣጫ መሆናቸው ተነሥቷል።
የብሔራዊ መረጃ እና ደኅንነት አገልግሎት በቀጣይ ዓመት እንደ ሀገር የሚከወኑ ሁነቶችን ተከትሎ ከውስጥ እና ከውጭ የሚሰነዘሩ የደኅንነት ስጋቶችን መቀልበስ የሚያስችል የሰው ኃይል፣ የቴክኖሎጂ እና የሎጀስቲክስ ቁመና ላይ እንደሚገኝ በመድረኩ መገምገሙን አገልግሎት መሥሪያ ቤቱ ለኢቢሲ በላከው መግለጫ አስታውቋል።
#ebcdotstream

1 year ago