Logo
Getu Temesgen
‹‹በጋዛ ጦርነት ኢትዮጵያዊ እስራኤላዊያን ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ ነው›› ተባለ
#ethiopia | ‹‹በጋዛ ጦርነት ኢትዮጵያዊ እስራኤላዊያን ትልቅ ዋጋ እየከፈሉ ነው›› ሲል እየሩሳኤሌም ፖስት ጋዜጣ ዘገበ፡፡ ትናንት ለንባብ በበቃው እየሩሳኤሌም ፖስት ጋዜጣ ላይ ያኮቭ ካትዝ የተባለው የጋዜጣው ባልደረባ በፃፈው ዘገባ ሰርጀንት ሻሀር ማኖቭ የተባለው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ለቤተሰቡ ኩራት የሆነ፣ ደስተኛና ብሩህ ህልም የነበረው ወጣት እንደነበር በመጥቀስ ጀምሯል፡፡

በጋዛ ወታደራዊ የኢንጂነሪንግ ክፍል ውስጥ በግዳጅ ላይ እያለ ታዛዥ፣ ደፋርና ብርቱ እንደነበርም አስረድቷል፡፡

ሌላኛው ሌተናልት ሻይ አየለ ከአራት ታናሽ ወንድሞች ያሉትና ፈገግታ የማይለየው እንደነበር ጠቅሷል፡፡ ወደጋዛ ከማቅናቱ በፊት ለቤተሰቦቹ በላከው ፎቶ ይህ ብሩህ ፈገግታው ቁልጭ ብሎ ይታይ እንደነበርም አስረድቷል፡፡

ፀሀፊው ሲቀጥልም ሰርጀንት ብርሀኑ ካሴ በኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ ወደእስራኤል የሄደው በዘጠኝ አመቱ እንደነበር አውስቷል፡፡ እንደጋዜጠኛው ገለፃ በጋዛ ጦርነት ህይወታቸው ካለፈ 889 የእስራኤል ወታደሮች መካከል እነዚህ 3ቱ ይጠቀሳሉ፡፡

ይሁንና በአጠቃላይ ለሞት የተዳረጉት ኢትዮጵያዊያን ቁጥር 40 መሆኑን ገልጿል፡፡ ጋዜጠኛው እንዳለው ኢትዮጵያዊያን ቤተ እስራኤላዊያን ከአጠቃላይ የእስራኤል ህዝብ መጠናቸው አንድ ነጥብ ሰባት ፐርሰንት ነው፡፡ ነገር ግን ከሞቱት የእስራኤል ወታደሮች ውስጥ አራት ነጥብ አምስት ፐርሰንቱን ይዘዋል፡፡ በመሆኑም ቤተእስራኤላዊያን በጋዛ ጦርነት ትልቅ ዋጋ መክፈላቸውን የጠቀሰው ዘገባው ይህ ማህበረሰብ እያጋጠመው ካለው ጫና ነፃ ሊወጣ እንደሚገባው አሳስቧል፡፡ #zehabesha

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.