የምግብ ምርቶች ማስታወቂያ ቁጥጥር ይደረጋል!
- የሚዲያ ተቋማትና አስተዋዋቂዎች ተጠያቂዎች ናቸው
#ethiopia | አዳማ — የኢትዮጵያ ምግብ፣ መድኃኒትና ጤና አገልግሎት ቁጥጥር ባለሥልጣን የምግብ ምርቶች ማስታወቂያ ለሕዝብ ከመሰራጨቱ በፊት በሕግና በሳይንሳዊ ማስረጃ ላይ የተመሠረተ፣ እውነተኛና አሳሳች ያልሆነ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል የማስታወቂያ ቁጥጥር መመሪያ መኖሩን አስታወቀ።
ባለሥልጣኑ በአዳማ ክሎቨርዴል ሆቴል ዛሬ ባዘጋጀው የሚዲያ ግንዛቤ መድረክ፣ የምግብ ምርቶች ማስታወቂያ ቁጥጥርን በተመለከተ ለሚዲያ አካላት ሰፊ ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የምግብ ምዝገባና ፈቃድ ባለሙያዋ ዳግማዊት ንጋቱ እንዳብራሩት፣ የማስታወቂያ አሰራጮች ከአስተዋዋቂዎች የሚቀበሉት መረጃ ትክክለኛነትና ማስታወቂያው የቁጥጥር መመሪያውን ማሟላቱን የማረጋገጥ ግዴታ አለባቸው።
በመመሪያው መሠረት የማስታወቂያ አሰራጭ ድርጅቶች በባለሥልጣኑ የተሰጠ ሕጋዊ የብቃት ማረጋገጫ ሊኖራቸው እንደሚገባና ባለሥልጣኑ በሚጠይቅበት ጊዜ ያስተላለፏቸውን ማስታወቂያዎች ቅጂና አስፈላጊ መረጃዎችን ማቅረብ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ያልተረጋገጡና የተጋነኑ የጤና ጥቅም ጥያቄዎች አይፈቀዱም
የምግብ ማስታወቂያዎች በተገቢ ሳይንሳዊ ማስረጃ ያልተደገፉ የጤና ጥቅም ወይም የፈውስ ተግባር እንዳላቸው አድርገው ማቅረብ እንደማይችሉ ተመላክቷል።
እንዲሁም “ብቸኛ”፣ “ለመጀመሪያ ጊዜ”፣ “ከዚህ ቀደም ያልነበረ”፣ “የሁሉም ምርጫ”፣ “ልዩ” እና “አንደኛ” የመሳሰሉ የተጋነኑ መግለጫዎች በተገቢው ማስረጃ ሳይደገፉ መጠቀም እንደማይፈቀድ ተገልጿል።
የአልኮል መጠጦች ማስታወቂያ ላይ ገደቦች
መመሪያው የአልኮል መጠጦች ለጤና ተስማሚ፣ ለማህበራዊ ስኬት ወይም ለአካላዊ ብቃት ጠቃሚ እንደሆኑ አድርጎ ማስታወቅን ይከለክላል።
በተጨማሪም ከ12 በመቶ በላይ የአልኮል ይዘት ያላቸው መጠጦችን ከቤት ውጭ ማስታወቂያ በስተቀር በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮና በሌሎች የሚዲያ አውታሮች ማስታወቅ ላይ ገደቦች መኖራቸው ተጠቁሟል።
ከዚህ ባለፈ አካለ መጠን ያልደረሱ ሕፃናትን በአልኮል ማስታወቂያ ላይ መጠቀም፣ በሕፃናት ፕሮግራሞች ላይ የአልኮል ማስታወቂያ ማስተላለፍና ከ12 በመቶ በላይ የአልኮል ይዘት ያላቸው መጠጦች አምራቾች ወይም ነጋዴዎች ፕሮግራሞችን ስፖንሰር ማድረግ እንደማይችሉ ተገልጿል።
የጨቅላ ሕፃናት ምግብ ማስታወቂያ
የጨቅላ ሕፃናት ምግብን በቴሌቪዥን፣ በሬዲዮ፣ በጋዜጣና በኢንተርኔት ጨምሮ በማንኛውም የሚዲያ መድረክ ማስታወቅ እንደተከለከለ ተብራርቷል።
በምርቶቹ ማሸጊያ ላይም ከእናት ጡት ወተት ጋር ማወዳደር ወይም “የማይተካ” የሚሉ መግለጫዎችን መጠቀም እንደማይፈቀድ ተጠቁሟል። በሽያጭ ቦታዎች ናሙና መስጠትና የዋጋ ቅናሽ ማስታወቂያ መለጠፍም ከተገደቡት ተግባራት መካከል ናቸው።
ሕፃናትን ያማከሉ ማስታወቂያዎች
ሕፃናትን ያማከሉ ማስታወቂያዎች የልጆችን ዕድሜና የማስተዋል ደረጃ ያገናዘቡ መሆን እንዳለባቸው ተገልጿል።
አንድ ምግብ የተጠቀመ ልጅ ካልተጠቀመ ልጅ በላይ የማህበራዊ ወይም የአእምሮ ብልጫ እንዳለው ማሳየትና ሕፃናት ፈጣን ምግቦችን ከመጠን በላይ እንዲወስዱ ማበረታታት እንደማይፈቀድ ተመላክቷል።
በተጨማሪም የግለሰቦችን ምስክርነት ወይም የግል ልምድ በመጠቀም ስለ አንድ ምግብ ጣዕም፣ ይዘት ወይም ጥቅም ማስታወቅ በመመሪያው የተገደበ መሆኑ ተብራርቷል።
ለሚዲያ ተቋማት የተሰጠው መልዕክት
የምግብ ምርት ማስታወቂያን ከማስተላለፍ በፊት ይዘቱ ከተደነገጉት የሕግና የቁጥጥር መስፈርቶች ጋር መጣጣሙን ማረጋገጥ የሚዲያና የማስታወቂያ አሰራጭ ተቋማት ኃላፊነት መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።
መመሪያው ከነሐሴ 2 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ የፀና መሆኑን የገለጸው ማብራሪያው፣ መመሪያውን በመጣስ የሚተላለፍ ማስታወቂያ ለሚያስተላልፉ አካላት ሕጋዊ ተጠያቂነት ሊያስከትል እንደሚችል አመልክቷል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#adama #media #foodregulation #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

5 days ago