Logo
Getu Temesgen
በባሌ ሐረና ደን የወፍ እንቁላል ብቻ የምትመገብ አዲስ የእባብ ዝርያ ተገኘች
#ethiopia | በኢትዮጵያ በባሌ ሐረና ተፈጥሮ ደን ውስጥ የወፍ እንቁላልን ብቻ ለምግብነት የምትጠቀም አዲስ የእባብ ዝርያ መገኘቷን ተመራማሪዎች ይፋ አደረጉ።

“ዳሲፔልቲስ አልቢጉላሪስ” (Dasypeltis albogularis) በሚል የሳይንስ ስም የተሰየመችው ይህች እባብ፣ እንደ ሌሎች ተመሳሳይ ዝርያዎች ሥጋ ወይም ነፍሳትን የማትመገብ ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ በወፍ እንቁላል ላይ ብቻ ተመሥርታ የምትኖር ናት።

እባቧ እንቁላልን በሙሉነቱ ከዋጠች በኋላ፣ ልዩ በሆነ የሰውነት ክፍሏ አሠራር አማካይነት የእንቁላሉን ቅርፊት ተፍታ የማስወገድ አስደናቂ ተፈጥሯዊ ችሎታ አላት።

በተጨማሪም ራሷን ከጠላት ለመጠበቅ የምትጠቀምበት ዘዴ የተለየ ነው። መርዝ በመርጨት ወይም በመንከስ ፈንታ፣ ቆዳዋን እርስ በእርስ በማሸት በሚፈጠር ድምፅ አዳኞቿን በማስፈራራት ራሷን ትከላከላለች።

የሳይንስ ተመራማሪዎች የዚችን እባብ ልዩ ማንነትና ዝርያ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለማረጋገጥ፣ ለሰባት ዓመታት ያህል ዘለቄታ ያለው የዘረመል (ዲኤንኤ) ምርመራና ጥልቅ ጥናት ሲያካሂዱ ቆይተዋል።

ይህ አዲስ ግኝት የባሌ ሐረና ደን ያለውን የብዝሃ ሕይወት ሀብትና የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ጸጋ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትኩረት እንዲያገኝ የሚያደርግ ትልቅ የሳይንስ ስኬት መሆኑ ተመልክቷል።
#bale #wildlife #nature #science #ethiopianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

12 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.