"ቱርክ በሁለቱም በኩል ልትጫወት ነው ወይስ አሰላለፏን ወደ ግብፅ እየቀየረች ነው?"
#ethiopia | የቱርኩ የጦር መሣሪያ አምራች ኩባንያ MKE በግብፅ ቅርንጫፉን ከፈተ።
ከቱርክ ግንባር ቀደም የጦር መሣሪያ አምራች ኩባንያዎች አንዱ የሆነው MKE በሰሜን አፍሪካ ትልቅ ገበያ በሆነችው ግብፅ "ዛፌር" የተሰኘ ቅርንጫፍ ኩባንያ ማቋቋሙን ይፋ አድርጓል።
ይህ ውሳኔ ኩባንያው ለቀጠናው አገራት የመከላከያና የጦር መሣሪያዎችን በጥራትና በፍጥነት ለማቅረብ ትልቅ ዕድል እንደሚፈጥርለት ገልጿል።
ይህ ጉዳይ በሰሜን አፍሪካ በባህረ ሰላጤው ሀገራት እና በአፍሪካ ቀንድ የጂኦፖለቲካዊ ሚዛን ላይ የራሱን ጥላ ማሳረፉ እየተነገረ ይገኛል።
ግብፅ የቱርክን የጦር መሣሪያ ቴክኖሎጂ በቅርበት ማግኘቷና በጋራ ማምረቷ በሰሜን አፍሪካና በአፍሪካ ቀንድ የምታሳድረውን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ተፅዕኖ ከፍ ያደርገዋል ተብሏል።
ይህ እርምጃ ሙሉ በሙሉ ከንግድና ከኢኮኖሚ ጥቅም ባሻገር ስትራቴጂካዊና ድብቅ አጀንዳዎች ሊኖሩት እንደሚችል የጂኦፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።
የቱርክ ወታደራዊ ቴክኖሎጂ በግብፅ በኩል ወደ ቀይ ባሕር ተፋሰስ መጠጋቱ በቀጠናው የባሕር ንግድ መስመር ላይ ተጨማሪ የኃይል አሰላለፍ ይፈጥራል ብለዋል።
የMKE በግብፅ መመሥረት በቀጥታ የንግድ እንቅስቃሴ ቢመስልም ከጀርባው ግን በቱርክ እና በግብፅ መካከል የተፈጠረውን አዲስ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት የሚያጠናክር መሆኑን ተንታኞች ተናግረዋል።
በተጨማሪም የአፍሪካ ቀንድ እና የቀይ ባሕር ቀጠናን ወታደራዊ ስትራቴጂ የሚቀይር አህጉራዊ ኩነት እንደሆነ ነው የተናገሩት።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #hornofafrica #redsea #militarynews #defenceindustry #zafer #tolga #eastafrica #middleeastpolitics

26 days ago