Logo
Getu Temesgen
አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ በብራሰልስ የዳይመንድ ሊግ የ5,000 ሜትር ሩጫ አሸነፈች
#ethiopia | በቤልጂየም ብራሰልስ አስተናጋጅነት በተካሄደው የ2026 ዳይመንድ ሊግ የ5,000 ሜትር የሴቶች ማጠቃለያ ውድድር አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ ድንቅ ብቃቷን በማሳየት የርቀቱ አሸናፊ ሆናለች።

አትሌት ፍሬወይኒ ውድድሩን በ14 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ ከ20 ማይክሮሴኮንድ በማጠናቀቅ የመጀመሪያውን ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

በዚህ የሩጫ መድረክ የድል መድረኩ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተያዘ ነበር።

አትሌት ልቅና አምባው በ14 ደቂቃ ከ36 ሴኮንድ ከ31 ማይክሮሴኮንድ ሁለተኛ በመሆን ስታጠናቅቅ፣ አትሌት ሰናይት ጌታቸው ደግሞ በ14 ደቂቃ ከ37 ሴኮንድ ከ09 ማይክሮሴኮንድ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ይህ ስኬት ለሀገራችን ሌላው ትልቅ ደስታና ኩራት ነው፤ አትሌት ፍሬወይኒ ሀይሉ፣ ልቅና አምባው እና ሰናይት ጌታቸው በብራሰልስ ዳይመንድ ሊግ የክብር መድረኩን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ አትሌቶች በመሸፈን ያስመዘገቡት ድል እጅግ የሚያስደስት ተግባር ሆኗል።

የውድድሩ የመጨረሻ ውጤት፡

1ኛ. ፍሬወይኒ ሀይሉ 14:35.20 ወርቅ
2ኛ. ልቅና አምባው 14:36.31 ብር
3ኛ. ሰናይት ጌታቸው 14:37.09 ነሐስ

አትሌቶቻችን ሀገራችንን በዓለም አቀፍ ስፖርት መድረክ በላቀ ጽናትና ብቃት ስላስጠሩ እንኳን ደስ አለን።
#diamondleague #athletics #brusselsdl #ethiopianathletics #freweynihailu #running #sport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.