Logo
Getu Temesgen
የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር የንግድና የኢንቨስትመንት ትስስርን የሚያፋጥን ጥናት በአለም አቀፍ መድረክ አቀረበ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ፌደራል ጠበቆች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መሠረት አያሌው ከአለም አቀፍ ንግድና ኢንቨስትመንት እድገት ጋር የተያያዘ ጥናታዊ ጽሁፍ በማዘጋጀት በውጭ ሀገር ንግግር አድርገዋል።

በዚሁ መድረክ ላይ የቀድሞው የማህበሩ ፕሬዝዳንት እና የኮሜሳ ፍርድ ቤት የመጀመሪያ ደረጃ ምድብ ዳኛ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው እንዲሁም የአሁኑ የማህበሩ ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ ደረሰ ተገኝተዋል።

ይህ ጥናት ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት እና ከሌሎች አለም አቀፍ የንግድ አጋሮቿ ጋር በሚኖራት ግንኙነት ወቅት የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በድርድር፣ በስምምነት እና በሽምግልና ለመፍታት የሚያስችል ነው።

በተጨማሪም የሀገሪቱን የንግድ መብቶች የሚያስከብር ሲሆን የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያዎችና ጠበቆች በአለም አቀፍ ደረጃ ያላቸውን ተሳትፎ እና ሚና ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።
#ethiopianbarassociation #ethiopianinvestmentcommission #comesa #internationaltrade #law #brics #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.