Logo
Getu Temesgen
“ኩላሊቴን አምጪ አሊያም 1.5 ሚሊዮን ዶላር ክፈይ!”
#ethiopia | የለገስኩሽን ኩላሊቴን መልሽልኝ ያለው የዶክተሩ አስገራሚ የፍቺ ክስ አነጋጋሪ ሆኗል።

በአሜሪካ ሎንግ አይላንድ የሚኖሩት የቀዶ ጥገና ሐኪም ዶ/ር ሪቻርድ ባቲስታ የባለቤታቸውን ዶኔልን ሕይወት ለማዳን ሲሉ አንዱን ኩላሊታቸውን በፈቃዳኝነት ለግሰው ነበር።

ነገር ግን ከሦስት ዓመታት በኋላ በትዳራቸው መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ዶኔል የፍቺ ጥያቄ አቀረበች።

በዚህ ጊዜ ታሪኩ ያልተጠበቀ አቅጣጫ ያዘ።

ዶ/ር ሪቻርድ ኩላሊቱን የሰጡት በትዳር ውስጥ እያሉ በመሆኑ አካሉ ተመልሶ እንዲሰጠው ወይም የገንዘብ ካሳ እንዲከፈለው ጠየቀ።

ዶክተሩ ለኩላሊቱ 1.5 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ጠየቀ።

ሕክምናዊ በሆነ መንገድ ኩላሊቱ ተነቅሎ እንደሚመለስ ባይጠብቅም የኩላሊቱ ዋጋ በትዳር ሀብት ክፍፍል ውስጥ ተካቶ ሊታሰብበት ይገባል የሚል ነበር።

ዳኛው የቀረበውን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አደረጉት።

ኩላሊቱ በፈቃደኝነት የተሰጠ ስጦታ እንጂ በገንዘብ ሊተመን የሚችል የጋራ የትዳር ሀብት ሊሆን እንደማይችል ወሰኑ።

በሕግ ታሪክ ከተመዘገቡት አስገራሚ የፍቺ ክርክሮች መካከል አንዱ የሆነው ይህ ጉዳይ በነፃ ፈቃድ የተሰጠ የሰውነት አካልን በሕግ ተከራክረው ማስመለስም ሆነ በገንዘብ ማስከፈል አይቻልም በሚል ውሳኔ ተጠናቋል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #divorcesettlement #doctor #donations #kidney #wife #divorce #surgeon #marriage

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.