Logo
Getu Temesgen
በወረቀት ላይ የቀረው የ78 አመቱ ድንጋጌ!

*የዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብቶች የመጀመሪያው ረቂቅ ድንጋጌ ይህንን ይመስል ነበር።
#ethiopia | በፈረንጆቹ 1948 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በፈረንሳይ ፓሪስ ተሰብስቦ ይህንን ታሪካዊ ሰነድ አጸደቀ።

ሰነዱ ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያስከተለውን ዘግናኝ እልቂትና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተከትሎ የተዘጋጀ ነበር።

ሁለተኛው የዓለም ጦርነት ያስከተለውን ዘግናኝ እልቂት ተከትሎ ከእንግዲህ በሰው ልጅ ላይ ግፍ አይፈጸምም በሚል መርህ የተረቀቀው ይህ ታሪካዊ ሰነድ ዛሬ 78 አመት ሞልቶታል።

በጦርነትና በመብት ጥሰት በታመሰችው ዓለማችን ውስጥ
በወረቀት ላይ የቀረ ሰነድ
ሆኗል በሚል ከባድ ትችት እየቀረበበትም ይገኛል።

ይህ ሰነድ የሰው ልጅ መሠረታዊ መብቶችና ነጻነቶች በመላው ዓለም ያለ ምንም ልዩነት እንዲከበሩና እንዲጠበቁ ጠንካራ መሠረት ጥሏል።

ድንጋጌው የሰው ልጅ ከተወለደበት ጊዜ ጀምሮ ሊኖሩት የሚገቡ መሠረታዊ የሲቪል፣ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ የማህበራዊ እና የባህል መብቶችን በዝርዝር ያካተተ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ ስምምነት ነው።

የሰነዱ መጸደቅ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ጭቁን ህዝቦች፣ ለነጻነት ታጋዮች እና ለሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች የትግል መነሻና የፍትህ መጠየቂያ መሳሪያ በመሆን ሰፊ ሚና ተጫውቷል።

ዘር፣ ቀለም፣ ጾታ፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት ወይም የፖለቲካ አቋም ሳይለይ እያንዳንዱ የሰው ልጅ በእኩልነትና በነጻነት የመኖር መብት እንዳለው አሳውቋል።

ይህ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌ የሰው ልጅ በታሪኩ ካስመዘገባቸው ታላላቅ ሁነቶች አንዱ ተደርጎ ይወሰዳል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #universal #declaration #humanrights #democracy #france #paris #inherited

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.