ታላቋ ኢትዮጵያን አሸናፊ የምናደርገው "የእኔ ሀሳብ ብቻ ይጽደቅ" ከሚል ግትር አቋም ስንወጣ ነው
*********************
በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ ለዘመናት የዘለቀው እና ዋነኛ ማኅበራዊ ፈተና ሆኖ የቆየው አካሄድ አሸናፊ እና ተሸናፊን ብቻ የሚያመርተው የጥሎ ማለፍ የፖለቲካ ባህል ነው።
ይህ አንዱ ወገን አሸንፎ የራሱን ፍላጎት ብቻ የሚጭንበት እና ሌላውን የሚያገልልበት አካሄድ፣ ዘላቂ ሰላምን ከመገንባት ይልቅ ቂምና በቀልን በማርገዝ ለተከታታይ ግጭቶች በር ሲከፍት ቆይቷል።
አሁን እየተካሄደ ያለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ግን ይህን አጥፊ ባህል በዘላቂነት የመቀየር ትልቅ ዓላማ አንግቧል።
አንዱ ሲያሸንፍ ሌላው የሚወድቅበትን ጎጂ ውድድር አስቀርቶ፣ ኢትዮጵያን ማዕከል ባደረገ መልኩ ሁሉም ዜጎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን የጋራ አሸናፊነት ማዕቀፍ ለመፍጠር እየሠራ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፥ ተሸናፊው ለከርሞ ግጭትን አርግዞ ስለሚመለስ እና አሸናፊውም ዘወትር ድሉን ለማስጠበቅ ስለሚታገል፣ ማንም ተሸናፊ የማይሆንበት እና የጋራ ሕልውና የሚረጋገጥበት ሀገራዊ ምክክር ትልቅ ዕድል ነው።
ይህን ታሪካዊ ኃላፊነት ከዳር ለማድረስ የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ነፃ እና ገለልተኛ ሆኖ የተመሠረተ በመሆኑ፣ መሠረታዊ የሆኑ ልዩነቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ሰፊ መዋቅር ዘርግቷል።
ኮሚሽኑ አካታችነትን፣ ግልጽነትን፣ ተዓማኒነትን፣ መቻቻልን እና የሕግ የበላይነትን መርህ አድርጎ መነሳቱ ለሀገራችን አዲስ የተስፋ ጭላንጭል ፈንጥቋል።
ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እስከ ታችኛው የወረዳ መዋቅር ድረስ የተዘረጋው የምክክር ሰንሰለት፣ ከ1 ሺህ 200 ወረዳዎች ሕዝባዊ አጀንዳዎችን በማሰባሰብ ለ4 ሺህ ተመካካሪዎች አቅርቧል።
የእነዚህ ተመካካሪዎች ስብጥር የፖለቲካ ፓርቲዎችን፣ ሲቪል ማኅበራትን፣ የሃይማኖት ተቋማትን፣ ሴቶችን፣ ወጣቶችን እና የዳያስፖራውን ማኅበረሰብ ያካተተ በመሆኑ ሂደቱን እጅግ አሳታፊ አድርጎታል።
በውይይቱ የሚነሱ በርካታ ሀሳቦችን እና ፍላጎቶችን በሥርዓት ለማስተናገድ ሲባል፣ ኮሚሽኑ አጀንዳዎችን በስምንት ዋና ዋና የጽንሰ-ሀሳብ አዕማድ ከፍሎ በሥራ ቡድኖች እያወያየ ይገኛል።
ከዚህም ባሻገር 120 አባላት ያሉት የማስማማት ቡድን በማቋቋም ከተለያዩ የሥራ ቡድኖች የሚነሱ ተቃራኒ ሀሳቦችን የማስተካከል፣ መደራረቦችን የማስቀረት እና ጽንፍ የያዙ ሀሳቦችን በማለዘብ ወደ አንድ የተቀናጀ ሀገራዊ ማዕቀፍ የማምጣት ጥበብ የተሞላበት ሥራ እየተከናወነ ነው።
በምክክሩ ሂደት ውስጥ የሁሉም ተሳታፊዎች ሀሳብ መቶ በመቶ ተቀባይነት ካላገኘ "ምክክሩ ከሽፏል" ብሎ ማሰብ ትልቅ ስህተት ነው።
የተለያዩ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ዳራ ያላቸው 4 ሺህ ሰዎች የሚያቀርቧቸው ፍላጎቶች በተፈጥሯቸው የሚቃረኑ ሊሆኑ ይችላሉ።
ሆኖም የምክክሩ ስኬት የሚለካው እያንዳንዱ ሀሳብ ሙሉ በሙሉ በመተግበሩ ሳይሆን፣ እርስ በርስ የሚቃረኑ ሀሳቦች ተጣርተው እና ተስማምተው ኢትዮጵያን የሚያሸጋግር የጋራ መሠረት መጣሉ ላይ ነው።
ይህ የስምምነት ግንባታ ሂደት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተካሄዱ ተመሳሳይ ምክክሮች ውጤታማነቱ የተረጋገጠ አሠራር ነው።
በሰፊ ሀገራዊ ምክክሮች ውስጥ መቶ በመቶ ምሉዕ ስምምነት ማግኘት በተግባር የማይቻል በመሆኑ፣ "ብቁ ስምምነት" የሚለው መርህ ተመራጭ የመፍትሔ ማዕቀፍ ሆኖ ያገለግላል።
ለዚህም ትልቅ ማሳያ የሚሆነው በደቡብ አፍሪካ የአፓርታይድ ሥርዓትን በሰላማዊ መንገድ ለማስወገድ በተደረገው ድርድር ወቅት የተተገበረው አሠራር ነው።
በወቅቱ ጥቂት ቡድኖች ሂደቱን ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት ተጠቅመው እንዳያስተጓጉሉ በማሰብ የዋና ዋና ባለድርሻዎች እና የብዙኃኑ ስምምነት ከተገኘ ሂደቱ ወደፊት እንዲገፋ ተደርጓል።
ይህ አካሄድ የደቡብ አፍሪካን ሕዝብ ከእርስ በርስ ጦርነት የታደገ አሻጋሪ ሕገ መንግሥት እንዲዘጋጅ እና ታሪካዊ ምርጫ እንዲካሄድ አስችሏል።
በኢትዮጵያም አሻጋሪ ሀሳብ ሊመጣ የሚችለው ተመካካሪዎች "የእኔ ሀሳብ ብቻ ይጽደቅ" ከሚል ግትርነት ወጥተው የሁሉንም ደኅንነት የሚያረጋግጥ ማዕቀፍ ሲቀበሉ ብቻ ነው።
ውይይትን ሊዘጉ ከሚችሉ ጽንፈኛ አቋሞች ይልቅ የዜጎችን መብት፣ ማንነት እና ደኅንነት በተሻለ ሁኔታ የሚያስጠብቁ መፍትሔዎች ላይ መወያየት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው።
በምክክሩ ያልጸደቁ ሀሳቦችም ቢሆኑ በነፃነት ተመዝግበው ለወደፊት የሕግ ማሻሻያዎች ማጣቀሻ ሆነው ያገለግላሉ።
ስለሆነም ዜጎችም ሆኑ መገናኛ ብዙኃን ይህን ሀገራዊ ምክክር እንደ ስፖርት ውድድር አንዱ አሸንፎ ሌላው የሚሸነፍበት አድርገው ከመገምገም መቆጠብ አለባቸው።
ይልቁንም ምክክሩ ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው ሥር የሰደዱ መዋቅራዊ ችግሮቻቸውን በጋራ የሚፈቱበት የሰላም እና የስምምነት ድልድይ እንደሆነ አድርገው ሊገነዘቡት እና በፅኑ ሊደግፉት ይገባል።
ምክንያቱም መጨረሻ ላይ ዋናዋ አሸናፊ መሆን ያለባት መተኪያ የሌላት ሀገራችን ኢትዮጵያ ናትና!
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #nationaldialogue #nationalconsensus #peacebuilding #ebc

2 months ago