Logo
Getu Temesgen
የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል የተዘረፈን ውድ አይፎን ስልክ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ አስመለሱ
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ ቦሌ ክፍለ ከተማ ጎሮ አደባባይ አካባቢ በትራፊክ መብራት ምክንያት ቆሞ ከነበረ ተሽከርካሪ ውስጥ በተቀናጀ ሴራ የተዘረፈ ውድ አይፎን 17 የስልክ ቀፎ በፖሊስ አባላት በተደረገ ፈጣንና የተቀናጀ ክትትል በ12 ሰዓታት ውስጥ ሊገኝ ችሏል።

የሰፈራ ፖሊስ የወንጀል መከላከል ኃላፊ ኢንስፔክተር ጥላሁን ቦንኬ የተባሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባል ባደረጉት የሚደነቅ የክትትል እንቅስቃሴ ወንጀሉ ከተፈጸመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስልኩን ተከታትለው ማስጣላቸው ተገልጿል።

የድርጊቱ ሰለባዎች የፖሊስ አባሉ ላሳዩት ፈጣን ምላሽ፣ የላቀ ሙያዊ ብቃትና የህዝብ አለኝታነት የከበረ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

ኢንስፔክተር ጥላሁን ቦንኬ አክለው ባስተላለፉት መልዕክት፣ አሽከርካሪዎች በትራፊክ መብራትና በትራፊክ መጨናነቅ ወቅት የጎን መስኮቶችን በመዝጋትና ንብረታቸውን በመጠበቅ በኩል አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
#bole #police #addisababa #iphone17 #traffic #ethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.