(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ዛሬ በስዊድኗ ጎተንበርግ ከተማ ፒኤስጂ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ከሚያደርገው የቅድመ-ውድድር (ፕሪ-ሲዝን) ጨዋታ አስቀድሞ፣ የፒኤስጂው አሰልጣኝ ሉዊስ ኤንሪኬ ለማንችስተር ዩናይትዱ ማይክል ካሪክ ማስጠንቀቂያ ምላሽ ሰጥተዋል።
ጋዜጠኛ "ማይክል ካሪክ እስካሁን በታላላቅ አሰልጣኞች ላይ እያደረገ ባለው ነገር (በሚያስመዘግበው ውጤት) ምክንያት ቡድንህን ይዘህ እንዳትመጣ አስጠንቅቆሃል፤ ለዚህ ምን ምላሽ አለህ?" ሲል ጠይቋል። ሉዊስ ኤንሪኬ ሲመልስም.... "ካሪክን እና እስካሁን ያደረገውን ሁሉ አከብራለሁ፤ ነገር ግን ትንሽ ከመጠን ያለፈ በራስ መተማመን ውስጥ የገባ ይመስለኛል። አዎ፣ ጥሩ የሚባሉ አሰልጣኞችን አሸንፎ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ነገ ሙሉ ለሙሉ የተለየ ፈተና ነው የሚጠብቀው።
"እሱ እንዳለው አለቃዬን (ፔፕን) ከኃላፊነቱ እንዲለቅ እንዳደረገው አውቃለሁ፤ ይህንኑ ለማረጋገጥም ለፔፕ ደውዬለት ነበር። እሱም 'አዎ፣ የካሪክ ኳስ (Carrick Ball) አደገኛ ነው' ብሎኛል። የካሪክን የጨዋታ አቀራረብ ተመልክቼዋለሁ፤ በጥንቃቄም አጥንቼዋለሁ። ትናንት ማታ እንኳን ጨዋታዎቹን ስመለከት አምሽቻለሁ... እውነቱን ለመናገር፣ ምን እያደረገ እንዳለ ይገባኛል። በእርሱ ላይ ተጫውቶ ማሸነፍ ቀላል አይደለም።
"ነገር ግን ለእርሱ አንድ መልእክት አለኝ፡ አትጨነቅ ማይክል! ቡድኔን ይዤ እመጣለሁ፤ ነገ ለእርሱ መጥፎ ቀን ይሆን እንደሆነ አብረን የምናየው ይሆናል። እሱ እና ሌሎች ታላላቅ አሰልጣኞች እንደሚሉት 'የካሪክ ኳስ' ያን ያህል አደገኛ ከሆነ፣ በፒኤስጂ ፊት መቆም ይችል እንደሆነ ነገ እናረጋግጣለን። ጎተንበርግ ላይ እንገናኝ! የካሪክ ኳስ ከ ፒኤስጂ (Carrick Ball vs PSG)።"

3 hours ago