እንኳን ለጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ፤አደረሰን🙏
ፍልሰታ የሚለው ቃል የተገኘው ፈለሰ ከሚለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን በጥሬ ትርጉሙ መለየት፣ ማረግ፣ ወደላይ መውጣት የሚለውን ትርጉም ይይዛል። ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ “ቅድስት ድንግል ማርያም ከሚያልፈው ዓለም ወደማያልፈው ዓለም፣ ከምድር ሕይወት ወደ ሰማያዊ ሕይወት፣ ተሻገረች” በማለት ፍልሰታ የሚለውን ቃል ትርጓሜ አመሥጥሮ ገልጾታል፡፡ ጾመ ፍልሰታ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋዋ ከሞትና መቃብር መለየትና ማረግን ያመለክታል። ይህ በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ከተወሰኑት ሰባቱ አጸዋማት ለዓመቱ የመጨረሻው ጾም ነው። እመቤታችን በዚህ ዓለም ለ64 ዓመታት ከኖረች በኋላ ጥር 21 ቀን 49 ዓመተ ምሕረት ዐርፈለች፡፡ ዕረፍቷም እንደሌላው ሰው በሕማምና በድካም አይደለም፡፡ በገነት ዕፀዋት መዓዛ ተመስጣ ቅድስት ነፍሷ ከሥጋዋ ተለይታለች፡፡
ቅዱሳን ሐዋርያት እመቤታችንን በአጎበር አድርገው ሊቀብሯት ወደ ጌቴሴማኒ ይዘዋት ሲሄዱ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና፣ ቀድሞ ልጇን ተነሣ ዐረገ እያሉ ሲያውኩን ኖረዋል፤ እርሷን ደግሞ ተነሣች ዐረገች እያሉ ሊያውኩን ነውና ኑ የማርያምን ሥጋ በእሳት እናቃጥለው ብለው ተነሱ፡፡ ከመካከላቸው አንድ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ ከሐዋርያት እጅ ለመንጠቅ ዘሎ ሄዶ የአልጋውን ሸንኮር ሲይዝ የታዘዘ መልአክ በረቂቅ ሰይፉ እጆቹን ቆረጠው፡፡ እጆቹም በአልጋው ሸንኮር ላይ ተንጠልጥለው ቀሩ፡፡ የምሕረት እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ቅዱስ ጴጥሮስ ጸልዮ እጆቹን እንዲመልስለት ነግራው እንደነበረ አድርጎለታል፡፡ መላእክት የእመቤታችን ሥጋዋን መላእክት ከዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር ወስደው አስቀምጠውታል፡፡ በስምንተኛው ወር በነሐሴ ሐዋርያት ቅዱስ ይህን በረከት አይቶ እኛ ሳናይ ቀረን ብለው ከነሐሴ 1 እስከ 14 ሁለት ሱባዔ ይዘው ከጌታችን ተቀብለው በጸሎትና በምህላ ቀበሯት።
ከአሥራ ሁለቱ ሐዋርያት አንዱ ቅዱስ ቶማስ ለሐዋርያዊ አገልግሎት ወጥቶ ነበርና ሲቀብሯት አልተገኘም። እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጇ ከሙታን ተነሥታ ስታርግ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ አገኛት። በዚህን ጊዜ ትንሣኤዋን ሌሎች ሐዋርያት አይተው እርሱ የቀረበት መስሎት “ቀድሞ የልጅሽን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ አሁን ደግሞ ያንችን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ” ብሎ ራሱን ከደመና ላይ ሊወረውር ቃጣው። እመቤታችን ከእርሱ በስተቀር ትንሣኤዋን ያየ አለመኖሩን ነግራ ግን ቶማስን አፅናናችው፡፡ ለምስክርነት እንዲሆንም በቀብሯ ጊዜ የነበረውን ሰበኗን ሰጥታው አረገች። ቅዱስ ቶማስም ኢየሩሳሌም ሲደርስ የእመቤታችን ነገር እንዴት ሆነ አላቸው፡፡ እነርሱም አግኝተን ቀበናት አሉት፡፡
እርሱም “ሞት በጥር፤ በነሐሴ መቃብር፤ ለሰሚውም አያምር፤ ይህ እንዴት ይሆናል?” ቢላቸው ቅዱስ ጴጥሮስ “ድሮም አንተ ተጠራጣሪ ነህ፤ ገንዘን የቀበረን እኛ እያለን እንዴት ትጠራጠራለህ” ብሎት ወደ መቃብሯ ሄደው መቃብሯን ቢከፍቱት ባዶ ሆኖ አገኙት፡፡ በዚህ ተደናግጠው ተያዩ፤ በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ “አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችን ተነሣች፤ ዐረገች፤ ይኸው ምልክቱ” ብሎ ገንዘው የቀበሩበትን ሰበን አሳያቸውና ሰበኗን ለበረከት ተካፈሉት፡፡ በዓመቱም ቶማስ ትንሣኤሽን አይቷልና እኛም በረከት አይቅርብን ብለው ከነሐሴ አንድ ጀምረው ሱባዔ ገቡ። ነሐሴ 16 ጌታችን እመቤታችን አምጥቶ ሐዋርያትን ቀድሶ አቁርቧቸዋል። ገዳውያን ይህን የጾም ወቅት ውዳሴዋንና ቅዳሴዋን በመጸለይ ያሳልፉታል፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

18 hours ago