ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የ2018 ዓ.ም የጾመ ፍልሰታ የሱባዔ መልእክት አስተላለፉ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ለ2018 ዓ.ም ጾመ ማርያም (ፍልሰታ) ባስተላለፉት የቡራኬና የሱባዔ መልእክት፣ ምእመናን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅና ፍቅርን በመተግበር ሱባዔውን እንዲያሳልፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው እግዚአብሔርን መውደድ በምናባዊ ነገር ሳይሆን ትእዛዙን በመጠበቅና ባልንጀራን ፤ መላውን የሰው ወገን እንደ ራስ አድርጎ በመውደድ የሚገለጽ መሆኑን ገልጸዋል።
ድንግል ማርያም ከአእላፋት መላእክት በላይ የምትበልጥ የአምላክ ማደሪያ በመሆኗ፣ ምእመናን በጾሙ ወቅት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅ እመቤታችንን ሊያከብሯትና በጸሎቷም ሊታመኑ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በ15ቱ የሱባዔ ወቅት የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የታመሙትንና የታሰሩትን በመጠየቅ እንዲሁም በንሥሐና በቅዱስ ቁርባን ማለፍ እንደሚገባ አዝዘዋል።
በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ ሥጋት የሆነውንና ፍጥረትን የሚያወድመውን ጦርነት እግዚአብሔር በኃይሉ እንዲያስቆም ምእመናን በሱባዔው ወቅት በትሑት ሰብእናና በቅን ልቦና እንዲጸልዩ አባታዊ አደራቸውን አስተላልፈዋል።
Seledadotio

2 days ago