(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ከተመሰረተው የሙስና ክስ መዝገብ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋለችውን የወ/ት ኢክራም አማን ገቲሶን ፎቶግራፍ ዛሬ በይፋ አውጥቷል። ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም ግለሰቧ በቁጥጥር ስር መዋሏን በዘገበበት ወቅት ፎቶዋን ማግኘት እንዳልቻለ መግለጹ የሚታወስ ሲሆን፣ ዛሬ ግን ፖሊስ ከሌሎች ተከሳሽ ባለስልጣናት ፎቶዎች ጋር አብሮ ይፋ አድርጎታል።
ወ/ት ኢክራም በሙስና መዝገቡ ላይ በዋነኝነት የተጠቀሰችው የተከሳሹ የአቶ ነቢል አንዋር የቅርብ ሰው በመሆን ነው። በክሱ እንደተመላከተው፣ ግለሰቧ ለአቶ ብርሃኑ አለቃ፣ ለአቶ ኤርሚያስ ተክሉ እና ለአቶ ነቢል አንዋር ከተለያዩ አካላት የሚሰበሰበውን የሙስና ገንዘብ በመቀበል ለአቶ ነቢል ገቢ ስታደርግ ቆይታለች።
በተጨማሪም ኤጀንሲዎችን በመክፈትና በመዝጋት ሂደት፣ እንዲሁም በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በኤጀንሲዎች እና በ'ELMIS' ሠራተኞች መካከል እንደ ደላላ በመሆን ከፍተኛ የገንዘብ ጥቅም ስታገኝ እንደነበር ተገልጿል።
በዚህ ህገ-ወጥ የደላላነት እና የገንዘብ ማሰባሰብ ተግባሯ፣ ወ/ት ኢክራም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በአዋሽ ባንክ በከፈተቻቸው ሶስት የተለያዩ የባንክ ሂሳቦች ውስጥ በአጠቃላይ 30,840,490.99 (ሰላሳ ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ ሺህ አራት መቶ ዘጠና ብር ከዘጠና ዘጠኝ ሳንቲም) ገቢ እንደተደረገላት የምርመራ መዝገቡ ያሳያል።
በዚሁ ከባድ የሙስና ወንጀል ጥቆማ መሰረት፣ ተጠርጣሪዋ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም. (17/11/2018 ዓ.ም) በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተደረገባት መሆኑን በዘ-ሐበሻ ዜና ከዚህ ቀደም መዘገባችን ይታወሳል።

2 days ago