Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ስፖርት) ጋዜጠኛው የቀድሞውን የማን.ዩናይትድ ተከላካይ ፓትሪስ ኤቭራን "አርሰናል ብሩኖ ጊማሬስን በ75 ሚሊዮን ፓውንድ ሲያስፈርመው እያየህ፣ ማንቸስተር ዩናይትድ ከዩሪ ቴሌማንስ ይልቅ እሱን ቢያመጣው ትመርጥ ነበር?" ሲል ጠየቀው።

ኤቭራ ሲመልስም.. "በፍጹም። ሰዎች ትኩረት የሚያደርጉት በተከፈለው የዝውውር ሂሳብ ላይ ብቻ ነው፤ እኔ ግን የምመለከተው ተጫዋቹን ነው። ቴሌማንስ እና ጊማሬስ እኩዮች ናቸው። ዩሪ አስቶንቪላን በሊጉ አራተኛ ደረጃ ይዞ እንዲያጠናቅቅ በጀግንነት ከረዳ በኋላ ነው በ35 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ እኛ የመጣው። የቡድናቸው ኮከብ ተጫዋች ከመሆኑም በላይ የዩሮፓ ሊግ ዋንጫን ማንሳት ችሏል። ይህ ለእኔ እጅግ አስደናቂ የዝውውር ስኬት እንጂ፣ በምንም መለኪያ መጥፎ ስራ አይባልም።

"በእርግጥ ዩሪ ዩናይትድን ሲቀላቀል 'እንኳን ደህና መጣህ' ለማለት ስልክ ደውዬለት ነበር። ለጥቂት ጊዜ አወራን፤ ሆኖም በንግግራችን መሀል የተናገራት አንዲት አረፍተ ነገር አእምሮዬ ውስጥ ታትማ ቀርታለች። 'ፓትሪስ... በመጨረሻም የልጅነት ህልሜ ወደሆነው ክለብ መጣሁ' አለኝ። በመቀጠል ግን ፈጽሞ ያልጠበቅኩትን ነገር አነሳ።

"'ከምንም በላይ ውስጤን በደስታ የሞላው ምን እንደሆነ ታውቃለህ?' ሲል ጠየቀኝ። እኔም 'ታላቁ ኦልድ ትራፎርድ ነው?' አልኩት። እየሳቀ 'አይደለም፣ ማይክል ካሪክ ነው' አለኝ።

ምክንያቱን ስጠይቀው እንዲህ ሲል መለሰልኝ፡

'ከኮቢ ማይኑ ጋር የሰራውን ተአምር ተመልክቻለሁ። ዩናይትድ የውድድር ዓመቱን እንዴት በሚገርም ብቃት እንዳጠናቀቀ አይቻለሁ። አንድ አሰልጣኝ አማካዮችን እንደ ማይክል ካሪክ በጥልቀት የሚረዳ ከሆነ... ከእሱ ጋር መስራት አለመፈለግ እብደት ነው የሚሆነው።'

ይሄኔ ነበር በደስታ ፈገግ ያልኩት። በአሰልጣኙ ላይ ሙሉ እምነት ያለው አማካይ፣ ዝም ብሎ ትልቅ ኮንትራት ከሚፈርም ተጫዋች እጅግ የላቀ ዋጋ አለው።"

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.