(ዘ-ሐበሻ ዜና) የሱማሊላንድ ፕሬዝደንት የኩላሊት ዲያሊሲስ አገልግሎት በነፃ እንዲሰጥ ትእዛዝ ሰጡ፡፡ የሱማሊላንድ ፕሬዝደንት አብዱራህማን መሀመድ ኢሮ በአገራቸው ውስጥ በነፃ የኩላሊት ዲያሊሲስ አገልግሎት እንዲሰጥ ትእዛዝ ማስተላፋቸውን ሂራን ኒውስ ዘገበ፡፡
እንደዘገባው ይህንን ትእዛዝ ለመስጠት የተገደዱት ህሙማን በቂ አገልግሎት ባለመኖሩ ለከፍተኛ ወጪ እየተዳረጉ መሆናቸውን በመግለፃቸው ነው፡፡ ትላንት ከሱማሊላንድ ፕሬዝደንት ፅህፈት ቤት የወጣው መመሪያ የአገሪቱ ጤና ሚኒስትር በአስቸኳይ 12 የዲያሊሲስ ማሽኖችን እንዲገዛና በሀርጌሳ አጠቃላይ ሆስፒታል የሚሰጠውን ይህንን ህክምና እንዲያሰፋ ትእዛዝ ማስተላለፉን ዘገባው አስረድቷል፡፡ ይህ የፕሬዝደንቱ መመሪያ ማንኛውም የኩላሊት ህመም ህክምና ዲያሊሲስን ጨምሮ በነፃ እንዲሰጥም የሚገልፅ ነው፡፡
ፕሬዝደንቱ ይህንን መመሪያ ከመስጠታቸው ከጥቂት ቀናት በፊት በሀርጌሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ተገኝተው ጉብኝት በማድረግ ከህሙማን፣ ከአስተዳደሩና ከዶክተሮች ጋር ውይይት አድርገው ነበር፡፡ ለዚህ ጉብኝት መሰረት የሆናቸው ደግሞ ባለፈው ሳምንት በርካታ የኩላሊት ህሙማን በሆስፒታሉ ግቢ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረጋቸው እንደሆነ ከዘገባው ላይ ተመልክተናል፡፡

4 days ago